ዓርብ 27 ፌብሩዋሪ 2015



ቢዮንሴና መናፍቃን/ፕሮቴስታንቶች/ ብታምኑም ባታምኑም
በኢየሱስ ስም የሚዋሸው ውሸት ይቁም
          ብታምኑም ባታምኑም ያልኩበት ምክንያት በናፍቃን እውነት ለማመን ስለሚያስቸግራቸው ነው
    ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል እንደሚባለው ብዙ ጊዜ በዚህ በፌስ ቡክ በተደጋጋሚ የምመለከተው መናፍቃን  እውነት እስከሚመስል ድረስ  የሚለቁት የሀሰት ክስ እንቅልፍ ከነሳኝ ሰነባብቷል ፡፡እንደሚታወቀው እነርሱ ከአባታቸው ከዲያብሎስ   የተማሩትን ውሸት በቤተክርስቲያን ላይ ማስተጋባት ከጀመሩ ሰነባብተዋል ፡፡
የዮሐንስ ወንጌል
844
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።

በውሸት ሰብኮ ሰውን ማሳመን የቤተክርስቲያን አላማዋም ተልኮዋም አይደለም ፡፡እውነት የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምህር ሆኖ በዚህ ምድር በሚመላለስበት ጊዜ እውነትን እንጂ ሀሰትን ሲሰብክ አልታየም ቤተክርስቲያንም ከጌታዋ በተማረችው ትምህርት እውነትን ያለሀሰት እየሰበከች እየተናገረች ትገኛለች፡፡ሁላችሁም ይህንን መልእክት የምታነቡ እህትና ወንድሞቼ ትዝ ይላችሁ ከሆነ በኢትዮጵያ  በ2000ዓ.ም/በሚሊኒየም/በአዲስ አመት መንግስት ህዝቡን እንዲያዝናኑ /እንዲያስጨፍሩ/ከጋበዛቸው የውጭ ዘፋኞች መካከል አንዷ ቢዮንሴ ናት፡፡ይህች ሴት በቤተክርስቲያን ተገኝታ ከቀድሞ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ጋር የተነሳችውን ፎቶ በዚህ በፌስ ቡክ በመለጠፍ  ‹‹ለሀጢያተኛዋ ዘፋኝ ታቦት ወጣላት ተዘመረላት ››እያሉ ቤተክርስቲያንን በሀሰት ሲከሱ ሲወነጅሉ አልፎ ተርፎም በአህዛብ/በእስላሞች/ ሲያሰድቡን እንዲሁም በባህር ላይ እንዳለ ኩበት የሚወላውለውን ስጋው/በድኑ/ አካሉ ቤተክርስቲያን መንፈሱ እነእርሱ አዳራሽ የሆነውን ‹‹አማኝ››ሲያጠራጥሩ ለተሀድሶ ክስ መንገድ ሲከፍቱ ተመልክተናል፡፡
     በመጀመሪያ ደረጃ እንድታውቁልኝ የምፈልገው ነገር ታቦት እንኳን ለዘፋኝ ለፓትርያሪክም እንደማይወጣ ታቦት የሚወጣው ለንግስ ጊዜ ብቻ እንደሆነ እና ቤዮንሴ በመጣች ጊዜ ታቦት እንዳልወጣና እንደማይወጣ ነው፡፡እንግዲህ ታድያ ቢዮንሴ ለምን በቤተክርስቲያን ተገኘች ቅዱስነታቸው ከእርሷጋር ለምን ተገኙ ለምንስ አብረው ፎቶ /ቪድዮ/ተነሱ/ተቀረፁ ፎቶ ላየይ እንደሚታየው ለምን ጥላ ወጣ ብላችሁ ለምጠይቁ እውነት ፈላጊዎች እውነቱ ይሄ ነው፡፡ቢዮንሴ ቤተክርስቲያን በተገኘች ጊዜ ቅዱስ ፓትርያሪኩ 17ኛ /በውል ባላስታውሰውም/የሲመት/የተሾሙበት/ፕትርክና/የተቀበሉበትን በአል እያከበሩ ነበር ፡፡እንደሚታወቀው በአለሲመት ሲከበር ጥላ ይወጣል የተሌዩ ሊቃውንት ያሬዳዊ ዜማ ያቀርባሉ ቅኔ ይቀኛሉ እግዚአብሔር ይህንን ስላደረገ ያመሰግናሉ ቢዮንሴም እንዳጋጣሚ በዛ በአል ላይ ስለተገኘች ከመንፈሳዊው በአል ተካፈለች እውነቱ ይሔ ሆኖ ሳለ እንዳባታቸው እንደዲያብሎስ በሀሰት ክስ ቤተክርስቲያንን እየከሰሱ አማኝ ያበዙ መስሎዋቸው በሰተንነታቸው እተጋለጡ ይገኛሉ፡፡
     እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነው እውነቱ ያ ሁኖ ሳለ የዛሬ7 አመት የተካሔደውን ጉዳይ ከ7 ዓመት በኋላ በውሸት ቀምመው ማቅረባቸው የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ሌላው ቢዮንሴ ዘፋኝ ሀጢያተኛ ሁና ሳለ እንዴት ቤተክርስቲያን ተገኝታ በአሉ ላይ ትሳተፋለች ቤተክርስቲያን ውጪ ሀጢያተኛ ነሽ ብላ ልታስወጣት ይገባ ነበር ብሎ የሚጠይቅ ይኖራል፡፡እንደሚታወቀው ቤተክርስቲያን ከጌታ ኢየሱስ በተማረችው ትምህርት መሰረት ሀጢያተኞችን ማግለል ሀጢያተኛ ናችሁ ብላ ከጌታ እንዲርቁ ማድረግ ሳይሆን በፍቅር አቅርባቸው የጌታን ፍቅር እንዲቀምሱ በዚያው ተማርከው እንዲቀሩ ታደርጋለች እንጂ እንደአይሁት ሀጢያተና ዘፋኝ ዘማዊ ናት በድንጋይ ተወግራ ትሙት እያለች መንግስቱን የምትከለክል አይደለችም ጌታ ሁሉን በፍቅር እንደቀረበ ለሀጢያተኛው ሲል እንደሞተ አይሁድ እንኳን ከሀጢያተኛ ጋር ይበላል ብለው ሲከሱት ከሀጢያተኛ እንዳልራቀ ሁሉ መናፍቃን/ዲያብሎሳውያን/ በሀሰት ክስ ቤተክርስቲያንን ቢከሱም ሀጢያተኖችን ሂዱ ከዚህ ብላ በዲያብሎስ ምክር የምታባርበት ምክንያት የለም በፍቅር ቀርባ ወደእግዚአብሔር ፍቅር እንዲገቡ በፍቅር ታስገድዳቸዋለች፡፡
የማቴዎስ ወንጌል
911
ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን። መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው።


የሉቃስ ወንጌል
152
ፈሪሳውያንና ጻፎችም። ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ።


     እንግዲህ ጌታኢየሱስን ለምን ቀራጩ ዘኪዮስ ቤት ገባህ ለምን ዘማዊቷ ሴት በድንጋይ እንዳትወገር ከለከልክ ለምን ከሀጢያተኞች ጋር ትበላለህ ትጠጣለህ ሀጢያተኖችንስ በፍቅር ለምን ትቀርባለህ ለሀጢያተኞች ለምን ሞትክ ብለው እንደማይጠይቁ ሁሉ በክርስቶስ ደም የተዋጀችውንም ቤተክርስቲያን ጌታዋን አብነት አድርጋ በምትሰራው ስራ ሊጠይቋት አይገባም ባይ ነኝ ፡፡የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን ፡፡
የዮሐንስ ወንጌል
810
ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ። አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት።

የዮሐንስ ራእይ
1210
ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።አሜን


የአብ ፀጋ የወልድ ቸርነት የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
ሻሎም/ሰላም/
                      ወንድማችሁ ሸዋፈራው አለነ ነኝ
በፀሎታችሁ አስቡኝ

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ