ኢየሱስ ማን ነው?
ይህንን ፅሁፍ ለመፃፍያነሣሣኝ የተለያዩ የፌስ ቡክ ጓደኞቼ የሚያስተላልፉት መልእክት ከመፅሐፍ ቅዱስ እውነታ ውጪ በመሆኑና የሚተረጉሙበት መንገድ ሰዎችን ወደእምነት የሚያመጣ ሳይሆን ይበልጥ እንዲጠራጠሩና የመጽሐፍ ቅዱስን እውነታ እንዲያውቁት ባለማድረጉ በተጨማሪ መፅሐፍ ቅዱሱን እርስ በርሱ እንዲጋጭና ሐዋርያት ስለኢየሱስ እውነተኛማንነት ያስተማሩትን የሚቃረን በመሆኑ ነው፡፡
ብዙዎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በራሳቸውና በመሰላችው መንግድ ሲገልጡት እናያለን፡፡ለብዙ ሀይማኖቶች መፈጠር ምክንያት የሆነውም ጌታ ኢየሱስን በትክክል ያለማወቅና ቅዱሳን ሐዋርያትና አባቶች ፅፈው ያለፏቸውን ስለኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ማንነት የሚገልጡ መልእክታትን በደንብ ያለመረዳትና ያለማመን ችግር ነው፡፡
መፅሐፍ ቅዱስን በራሳችን መንገድ ተርጉመን መረዳት አንችልም ምክንያቱም የተፃፈው እንደስጋዊ ፍቃድ በስጋ ምርምር ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሰዎች አማካኝነት ነው፡፡በታሪክም እንደምናውቀው ብዙዎች በራሳቸው መንገድና በስጋዊ ፍልስፍና ተመርተው ለመተርጎም ስለቃጣቸው ወርቀው እንደቀሩ ነው፡፡እስቲ ከጥንት የቤተክርስቲያን ታሪክ በስጋዊ ፍቃድ መፅሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም ፈልገው ያልሆነ ኑፋቄ ውስጥ ገብተው የቀሩትን ቤተክርስቲያንም አውግዛ የለየቻቸውን ሰዎች በጥቂቱ እንመልከት፡-
1.ጉባኤ ኒቂያ ፡
-በዚህ ጉባኤ የተሳተፉት አለማቀፍ አባቶች - 318
-ኑፋቄ-ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ነው
-ይህንን ክህደት ያነሳሳው/ከሐዲው/- አርዮስ የሊቢያ ተወላጅ ሲሆን የእውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን ካሃን ነበር
-አመተ ምህረት- 325
-318ቱ አለም አቀፍ አባቶች ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ሳይሆን የፍጡራን ፈጣሪ መሆኑን ከመፅሀፍ ቅዱስ ጠቅሰውና ተከራክረው ረተው አውግዘው ከቤተክርስቲያን ህብረት ለይተውታል፡፡
2.ጉባኤ ቁስጥንጥንያ
-በዚህ ጉባኤ የተሳተፉት አለማቀፍ አባቶች - 200
-ኑፋቄ መንፈስ ቅዱስ አካል የሌለው ፍጡር ነው
-ይህንን ክህደት ያነሳሳው/ከሐዲው/-መቅዶንዮስ
-አመተ ምህረት- 381
-200ቱ አለም አቀፍ አባቶች መንፈስቅዱስ ፍጡር ሳይሆን የፍጡራን ፈጣሪ ከሶስቱ አካላት አንዱ መሆኑን ተከራክረው ረተዋል መናፍቁንም አውግዘዋል፡፡
3.ጉባኤ ኤፌሶን
-በዚህ ጉባኤ የተሳተፉት አለማቀፍ አባቶች - 150
-ኑፋቄ - ኢየሱስ ሁለት አካል ሁለት በሐሪ ነው፡፡እመቤታችን የሰው እናት እንጂ የአምላክ እናት አይደለችም፡፡
-ይህንን ክህደት ያነሳሳው/ከሐዲው/-ንስጥሮስ ሊቀጳጳስ
-አመተ ምህረት- 431
-150ቱ አለም አቀፍ አባቶች ጌታ አንድ አካል አንድ በሀሪ በተዋህዶ መሆኑን እመቤታችንም የአምላክ እናት መሆኗን ተከራክረው ረተዋል መናፍቁንም አውግዘዋል፡፡
ማሳሰቢያ፤-ከእነዚህ ጉባኤያት ውጪ ያሉትን አራቱን ጉባኤያት አምስቱ እህት አብያተክርስቲያናት/ኢትዮጵያ፡ግብፅ፡ሶርያ፡አርመን፡ሕንድ/ አይቀበሉም፡፡ምክንያቱም ኑፋቄ ስለሆነ፡፡
ወደፊት ስለነዚህ ጉባኤያት በሰፊው እናያለን
ኢየሱስ ማን ነው?
1.የይሖዋ ምስክሮች፡-መጀመሪያ የተፈጠረ መንፈሳዊ የእግዚአብሄር/ይሖዋ/ ፍጡር፤የእኛ አማላጅ፤ተፈጥሮ ሌላ ፍጥረታትን የፈጠረ፤የእግዚአብሔር ልጅ……..
2.እስልምና፡-ከደጋግ ነቢያት አንዱ ያልሞተ ያልተነሳ ……..
ጌታስ በድንግልናተፀንሶ በድንግልና የተወለደ የሞተ የተነሳ አምላክ የነቢያት ጌታ ነው
3.ፕሮቴስታንት፡-አዳኝ፤አማላጅ/ለማኝ/፤ጌታ፤እግዚአብሄር፤ፈራጅ/አንዳንዶቹ ፕሮትስታንቶች/………
እዚህ ጋር የፕሮቴስታንቶቹ አስተምህሮ እርስ በርሱ የሚጋጭ ነው፡፤ምክንያቱም አዳኝ ብለው ካመኑ ያድነናል እንጂ ያማልደናል ማለት የለባቸውም ማዳን የሚችል ያድናል በራሱ እንጂ አያማልድም፤ጌታ ነው ከተባለ ባሪያ እንጂ ጌታ አይማልድም፤እግዚአብሔር ነው ካሉም እግዚአብሔር ማማለድ ባህሪው አይደለም……………
4.ካቶሊክ፡-ጌታ፤አዳኝ፤እግዚአብሄር፤በስጋው የሚማልድ፤አንድ አካል አንድ በሀሪ……..
5.ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፡-
ኢየሱስ ክርስቶስ፡-
-እግዚአብሔር፤ፈጣሪ፤አምላክ ነው፤-ዮሐ 1፡1-4፣ሮሜ 9፡1-5፣ኤፌ 2፡10፣ቆላ 1፡15-20፣ዕብ 1፡1-4፣2ጴጥ 1፡1፣1ዮሐ 5፡20-21፣ቲቶ 2፡11-14 በብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሔር የተነገሩ ትንቢቶች በኢየሱስ ተፈፅሟል ስለዚህ እግዚአብሔር ነው፡፡
-ሰውም አምላክም/ሰው የሆነ አምላክ/ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ በተዋህዶ/፤አራቱም ወንጌላት ላይ የተፃፈውን የጌታ ህይወት ብንመለከት ሰው የሆነ አምላክ እንደሆነ ይገልፅልናል፡፡ለምሳሌ፤-ተርቧል አምስት ገበያህዝብ መግቧል፤ተጠምቷል የህይወት ውሀ እንደሆነ ተናግሯል፤ፀልዩአል ፀሎትን ተቀብሏል፤ሞቷል ተነስቷል…….እነዚህን መለኮታዊና ስጋዊ በሀርያት በአንዱ በክርስቶስ በተዋህዶ ተንፀባርቀዋል፡፡አራቱን ወንጌላት ይመልከቱ
-አዳኝ ፤የህይወት ውሃ፤መንገድ፤እውነትና ህይወት ነው፡- በሞቱ ሞትን ሽሯል፤ቤዛ ሁኖ ደሙን አፍሶ ክሶናል ፤እርሱን በማመን ወደድህነት እንድንቀርብ አድርጎናል፤ለዘላለም እንዳንጠማ የሕይወት ውሀ ሆኖልናል፤ህይወት ሆኖናል፤ከጨለማ ወደብርሃን አሸጋግሮናል፤በደሙ ዋጅቶናል፤እርሱን በማመን አፅንቶናል……….
-ጌታ ነው፤-የጌቶች ጌታ የአማልክት አምላክ የነገስታት ንጉስ ነው፡፡እንሰግድለታለን እናመልከዋለን፡፡
-ከአባቱ ጋር የተስተካከለ ነው፡-ዮሐ 14፡8-10፣ዮሐ 17፡4፣ዮሐ 10፡30፣ዮሐ 5፡18፣ዮሐ 10፡33፣ቆላ 2፡9፣ፊል 2፤1-7፣1ጢሞ 3፡16፣ሚክ5፡2
-ፈራጅ ነው፡-ዮሐ 5፡22-27፣ዮሐ 9፡39፣2ጢሞ 4፡1፣2ጢሞ 4፡7-8፣ሐዋ10፡42፣ሐዋ 17፡31፣ሮሜ 14፡10፣2ቆሮ 5፡10፣ማቴ 16፡26-27፣ዳን 7፡9-10፣ማቴ 25፡31 ራእይ ዮሐንስ ሙሉውን ስንመለከት ጌታችን ለፍርድ እንደሚመጣና በዚ አለም እንደሚፈርድ ይነግረናል፡፡ ማራናታ/ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና/አሜን
‹‹ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን››
የሐዋርያት ስራ 10፡42
ሐዋርያት የታዘዙት ጌታ ኢየሱስ ፈራጅ እንደሆነ እንዲመሰክሩ እንጂ አማላጅ ብለው እንዲናንቁት አይደለም
-የሞተ፤የተነሳ፤በክብር ያረገ፤ዳግም ለፍርድ የሚመጣ
የኢየሱስ አገልግሎት፤-
-ነፍሱን በመስጠት አገልግሏል፡-ማቴ 10፡45፣ፊል 2፡6-8፣1ዮሐ 3፡16፣ዮሐ 10፡11፣15፡13
-ቤዛ በመሆን አገልግሏል፡-ማር 10፡45፣ኤፌ 1፡7፣1ጢሞ 2፡6
-መስዋት በመሆን አገልግሏል፡-ዕብ 10፡1፣ኤፌ 5፡2፣1ቆሮ 5፡7
-የበደላችን ስርየት ነው፡-ዕብ 9፡22፣1ዮሐ 1፡7
-የእዳ ደብዳቤያችንን ደመሰሰው፡-ቆላ 2፡14
-የክስ መዝገባችን ተዘግቷል፡-ቆላ 2፡13
-ሊቀ ካህናት በመሆን አገልግሏል፡-ዕብ 9፡13
-የህይወት መንገድ መርቆ ከፍቶልናል፡-ዕብ 10፡19-22
-ደሙን በማፍሰስ አገልግሏል፡-1ዮሐ 1፡7……………….አድኖናል
ስለኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ያላት እምነት ይህ ብቻ ዐይደለም ቤተክርስቲያን ገብታችሁ ተማሩ
ማጠቃለያ
እንግዲህ ከዚህ ውጪ የቤተክርስቲያን ትምህርት የለም፡፡
ማስተካከያ ካለ እቀበላለው
ማራናታ
እህቴ ጌታ ኢየሱስ አንድ ጊዜ ምልጃን ፈፅሞ በምድር ላይ ሔዷል ዛሬም ይማልዳል ማለት ሞኝነት ነው

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ