ምክር ለሙስሊሞች /ለመሀመዳውያን/
በዚህ በፌስ ቡክ ብዙ ጊዜ በመፅሐፍ ቅዱስ እና በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ዙሪያ የኢየሱስ አማኞች የሆነውን በክርስቶስ ስሙ
ክርስቲያን የተባልነውን ጥያቄ ትጠይቃላችሁ ፡፡ ለጥያቄያችሁም በቂ መልስ ስንሰጣችሁ የመፅሐፍ ቅዱስ እና የኢየሱስ አማኞች እኛ
ሁነን ሳለ ራሳችሁን መፅሐፍ ቅዱስን እንደተረዳ እና ስለኢየሱስ ማንነት አዋቂ አድርጋችሁ በመቁጠራችሁ ምክንያት የሰጠናችሁን መልስ
ባለመቀበል የመፅሐፍ ቅዱሱን ትርጓሜ ይህ አይደለም አንቀበላችሁም ይህ ክፍል ለመናገር/መልእክት ለማስተላለፍ/የፈለገው እንዲህ የሚል
ነው እያላችሁ በኮሜንት አስተያየታችሁን ስትሰጡ አያለሁ፡፡በመሰረቱ መፅሐፍቅዱስን የምናምነው እኛ እንጂ እናንተ አይደላችሁም ስለመፅሐፍ
ቅዱስም ትርጉም የምናውቀው እና እንጂ እናንተ አይደላችሁም ፤ስለኢየሱስ ማንነት መናገር ያለበትም አማኙ እንጂ ፍፁም ክህደት ያለባችሁ
እናንተ አይደላችሁም ፡፡ስለዚህም የፈለጋችሁትን በኢየሱስ ላይም ሆነ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ ብሎም በእምነታችን ላይ ጥያቄ መጠየቅ
ትችላላችሁ የምንሰጣችሁን መልስ በጥሞና አዳምጣቹ/አንብባቹ/ ወደእውነቱ ከመምጣት ይልቅ ትችት ውስጥ መግባት አስፈላጊ አይደለም
ባይ ነኝ ፡፡
የክርስቶስ ሰላም ከናንተጋር ይሁን
ወንድማችሁ ሸዋፈራው አለነ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ