እመቤታችን ፍጹም ስው ናት !!!
ካቶሊካውያን ወላዲት አምላክ ድንግል ማርያምን "ሀይል አረማዊት" ማለታቸው እርሳን ያከበራት መስላቸው ነው ። ይሁን እንጂ እመቤታችን ፍጹም ስው ናት ። ምክንያቱም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአብርሃም ከዳዊት የተገኘች የቅዱስ እያቄምና የቅድስት ሐና ልጅ ናትና። ለዚህም የሚከተለውን ማስረጃ በመመልከት ከስው ወገን መሆናን በሚገባ ማረጋገጥ ይቻላል ።
ሀ) እነሆ ዘመድሽ አልሳቤጥ መባላ ። ሉቃ 1፤ 35
ለ)ጌታ የነሳው የአብርሀም ስጋ መሆኑን ። ዕብ 2፤16
ሐ) የአንድ ልጃ የኢየሱስ ከርስቶስ የዘር ሀረግ ሲቆጠር ከሰዎች ወገን መቆጠሩ ። ማቴ 1፤ 1

በጠቅላላ እየሱስ ክርስቶስ የስው ልጅ መባሉ እርሳ ከስው ወገን በመሆና እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም። ማቴ
16፤13 ። ከእግዚአብሔር የተላከ ቅ/ገብርአል እና መንፈስ ቅዱስ አድሮባት የምትኖር ቅድስት አልሳቤጥም « አንቺ
ከሴቶች መካከል የተለየሽ የተባረክሽ ነሽ » አላት እንጂ «ሀይል አረማዊት » አላላትም። ሉቃ 1፤ 26-42
በዚህም መስረት እኛ እመቤታችንን የምንማፅናት ከእግዚአብሔር አስተካክለንም አነፃፅረንም አይደለም ። ከቀድሞ ጀምሮ አባቶች ስለእመቤታችን የሚያስተምሩን « እርሳ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ደግሞ በላይ ናት» ብለው ነው ። ስለሆነም በመዝሙራችንም ሆነ በፀሎቻችን ፤ ብሎም በቅዳሴያችን ስማን ከስመ ስላሴ ቀጥለን እንጠራለን ።
በነገረ ድህነትም እመቤታችን ቅ/ድንግል ማርያም ለመዳናችን ምክንያት ሆነች ። እንላለን እንጂ «ከጌታ ጋር አዳነችን » አንልም። « ምክንያተ ድህኒ » የምንላትም ለእግዚአብሔር የማዳን ስራ መሳሪያ ሆና በመገኘታ ነው ። ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ፃለምን ለማዳን ሲል በመስቀል ላይ የቆረሰው የእርሳን ስጋ ፤ ያፈሰስውም የእርሳን ደም እንዲሁም በፍቃዱ አሳልፎ የስጠው ነፍስ ከእመቤታችን የነሳው ነፍስ ነው ። ስለሆነም የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ በምንናገርበት ጊዜ እመቤታችንን አንለያትም ። ምክንያቱም ወልዳ ያስገኘች ፤ አዝላ የተስደደች ፤ በሚያስተምርበት ጊዜ ከሀገር ሀገር አብራ የተንከራተተች ፤ በተስቀለበት እለትም ከእግረ መስቀሉ ስር የተገኝች ናትና ። አሁንም ያለችው በቀኙ ነው ። መዝ 44፤ 9። በምልጃዋም ታድነናለች ። እግዚሃብሔር በማይመረመር ጥበቡ ለፃለም ድህነት ምክንያት ትሆን ዘንድ ያስቀራት ንጽህት ዘር እመቤታችን ናት ። ኢሳ 1፤ 9
በመሆኑም ፃለም ሁሉ ለዳነበት ምሥጢር መፈጸሚያ መቅደስ ፤ ለመለኮት ማደሪያ ሆነች ። በስዎች ላይ ስልጥኖ የነበረውን የጨለማ ገዚ ዲያቢሎስን ድል ነስቶ አዳምን ከሲኦል ባርነት ነፃ ያወጣ ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሳም ነፍስ ነስቶ ከእርሳ ተወለደ ። ተወልዶም አዳነን ።
«የመዳናችን ምክንያት» በመሆና በኦርቶዲክሳዊ ልጆቻ ዘንድ እመቤታችን ልዩ ስፍራ አላት ። ይቆየን !!!

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ