ዓርብ 27 ፌብሩዋሪ 2015



ይድረስ ለፕሮቴስታንቶች
መጽሐፍ ቅዱስ እና መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የሚለው አስተምህሮ
SOLA SCRIPTURA
ከተሐድሶ /Reformation/ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ፕሮቴስታንቶች መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ (Sola Scriptura) የሚል መመሪያ መከተል ጀመሩ፡፡ ነገር ግን ይህ መመሪያ ራሱ በየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ አይገኝም፡፡
ይህ ነገር ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ከተፈለገ (ማለትም ከቤተ-ክርስቲያን ሕያው የትውፊት ምስክርነት፣ ከቤተ-ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን የመተርጎም ሥልጣን እና ስጦታ በተለየ ወይም እነዚህን ሳንመለከት ለመዳን አስፈላጊ ሆነው ለእግዚአብሔር የተገለጡት ነገሮች ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ተጠቃለው ይገኛሉ ካልን) Sola Scriptura ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የሚለው አስተምሕሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጦ መገኘት ነበረበት፤ ነገር ግን ይህ በየትኛውም ክፍል አይገኝም፡፡
ከዚህ አስተምሕሮ በተቃራኒ መጽሐፍ ቅዱስ በየትኛውም ቦታ ለክርስቲያኖች ዋነኛ፣ በቂ እና ሌላ ተጨማሪ ድጋፍ የማያስፈልገው (በርካታ ፕሮቴስታንቶች እንደሚያስቡት) የእምነት መመሪያ ስለመሆኑ አያብራራም፡፡ ይልቁም መጽሐፍ ቅዱስ የራሱን አስፈላጊነት እና ሥልጣን እንዲሁም የተቀደሰውን ትውፊት እና የቤተ-ክርስቲያንን አስፈላጊነት እና ሥልጣን ይገልጻል፡፡ ማቴ.16፡18-19 ‹‹እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚህችም ዐለት ላይ ቤተ-ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆች አይችሏትም፡፡ የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፡፡ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል፡፡›› 
ማቴ.18፡17-18 ‹‹ደግሞም ቤተ-ክርስቲያንን ባይሰማት እንደ አረመኔ እና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ፡፡ እውነት እላችኋለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፡፡ በምድርም የምትፈቱት በሰማያት የተፈታ ይሆናል››
ሉቃ.10፡16 ‹‹የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል፡፡››
መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ Sola Scriptura (መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ) የሚለውን መመሪያ እንደማያስተምር ነቅሰው በማውጣት ከሚያሳዩን የአዲስ ኪዳን ክፍሎች በተጨማሪ ‹‹የካህናትን›› የማስተማር ሥልጣን አንቀበልም የሚሉ እና ከእግዚአብሔር ሥልጣን ለተሰጣቸው ለእነዚሁ ካህናት የማይታዘዙትን በሚመለከት በብሉይ ኪዳን የማስጠንቀቂያ ቃል እናገኛለን፡፡ በዚህ የብሉይ ኪዳን ክፍል እንደምናገኘው እግዚአብሔር ካህናቱ ሕጉን (ሃይማኖታዊ ሕግ፣ ማህበራዊ ሕግ፣ የወንጀል ሕግ) ይተረጉሙ ዘንድ የሚያስችላቸውን ሥልጣን ሰጥቷቸዋል (ዘሌ.20፡1-27፣         )፡፡
ይህም ሥልጣን በሕጉ ትርጓሜ ላይ ተመሥርተው የመወሰን እና የመፍረድ ሥልጣን ጭምር ነው፡፡ ዘዳ.17፡8-13 ‹‹በደም እና በደም በፍርድ እና በፍርድ በመቁሰል መካከል በአገርህ ደጅ ውስጥ ስለሚከራከሩት ክርክር የሚሣንህ የፍርድ ነገር ቢነሣ አንተ ተነሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደመረጠው ሥፍራ ትወጣለህ፤ ወደ ሌዋውያን ካህናት በዚያም ዘመን ወደ ተሾመው ፈራጅ መጥተህ ትጠይቃለህ፤ እነርሱም የፍርዱን ነገር ይነግሩሃል፡፡ እግዚአብሔርም ለመረጠው ሥፍራ የነገሩህን የፍርድ ነገር ታደርጋለህ፤ እንዳስተማሩህም ታደርግ ዘንድ ጠብቅ፡፡ እንዳስተማሩህም ሕግ እንደነገሩህም ፍርድ አድርግ፤ ከነገሩህም ፍርድ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፡፡ ማናቸውም ሰው ቢኮራ፤ በዚያም አምላክህን እግዚአብሔርን ለማገልገል የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ለመስማት ባይወድድ ይሙት፡፡››
ከዚህ ጋር በተመሳሳይ ከላይ ያየናቸው ክፍሎች ለይተው እንዳስቀመጡት እግዚአብሔር የካህናትን ሥልጣን በማስተማር (ማቴ.28፡20)፣ መጽሐፍ ቅዱስን በመተርጎም (የሐ.ሥ.2፡14-36) በማሰር እና በመፍታት (ማቴ.18፡18፣ የሐ.ሥ.15፡28-29) እናም ደግሞ በእርሱ ስም በተሰጣቸው የማስተማር ሥልጣን ቀብቷቸዋል (ሉቃ.10፡16)፡፡
ይሁዳ 10-11 ‹‹እነዚህ ሰዎች ግን ለማስተዋል ያቃታቸውን ነገር ሁሉ ይሳደባሉ፤ አዕምሮ እንደሌላቸው እንስሶች በተፈጥሮ ስሜት የሚያውቁት ነገር ቢኖር እንኳ በእርሱ ይጠፋሉ፡፡›› ካለ በኋላ በጣም ጠንከር ባለ ድምፅ እንዲህ ያስጠነቅቃል ‹‹በቃየል መንገድ ስለሄዱ፣ ለገንዘብ ብለው በበለዓም ስህተት ስለወደቁ፣ ቆሬም እንደተቃወመ ስለተቃወሙ በመቃወማቸው ስለጠፉ ወዮላቸው!›› (11.12)
‹‹የቆሬ ዐመጽ›› (ቆሬ የአብርሐም የልጁ ልጅ ነበር) ብሎ ይሁዳ የሚናገረው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኦሪት ዘኁልቅ 16፡1-35 የተገለጸው ነው፡፡ ቆሬ እና ወገኖቹ ሕጋዊና ተገቢ በሆነው በሙሴ እና በካህናቶቹ ሥልጣን ላይ አምጾ ነበር፡፡
ሌሎች የተጠቀሱ ቦታዎች፡- 1ኛቆሮ.10፡8፣ 1ኛቆሮ.11፡2፣ 1ኛተሰ.2፡13፣ 1ኛተሰ.2፡15፣ 1ኛ ጢሞ.3፡14-15፣ 2ኛጴጥ.3፡15-17፣ 2ኛጴጥ.1፡20-21፣ 2ኛጴጥ.2፡1
‹‹የእግዚአብሔር ቃል›› ማለት ሁልጊዜ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ›› ብቻ ማለት አይደለም
አንዳንድ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹የእግዚአብሔር ቃል›› የሚለውን አገባብ መጽሐፍ ቅዱስን ለማለት የገባ አድርገው ያስቡታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ግን እንደዚያ ለማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ኢየሱስን፣ በቃል የሚተላለፈውን ስብከተ ወንጌል፣ የመልእክትን ቃል ጭምር ያሰማል።
ኢሳ.55፡10-19 ‹‹ዝናብ እና ደቂቅ በረዶ ከሰማይ ወርደው ምድርን በማርካት ፍሬ እንደምታፈራ እንደሚያደርጋትና ለዘሪው ዘርን፣ ለበላተኛውም ምግብን ሳይሰጡ ወደ ሰማይ እንደማይመለሱ ከእኔ አንደበት የሚወጣውም ቃል እንደዚሁ ነው፡፡ እርሱ የላክሁትን ጉዳይ ሳያከናውንና ተልዕኮውን ሳይፈጽም ወደ እኔ አይመለስም፡፡››
ሉቃ.3፡2-3 ‹‹በዚህ ጊዜ የዘካሪያስ ልጅ ዮሐንስ በበረሐ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ፡፡ ስለዚህ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ባሉት አገሮች ዙሪያ ‹ለኃጢአታችሁ ይቀርታ እንድታገኙ ንስሐ ገብታችሁ ተጠመቁ› እያለ ያስተምር ነበር፡፡››
ሌሎች የተጠቀሱ ቦታዎች፡- ሉቃ.4፡44፡5፡1፣ 1ተሰ.2፡13፣ ሉቃ.8፡11-15፣ ዕብ.4፡12-13፣ ዮሐ.1፡1፣14፣ ዕብ.11፡3፣ የሐ.ሥ.4፡31


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ