ማክሰኞ 24 ፌብሩዋሪ 2015

 በኢየሱስ ክርስቶስ ታምናለህ; እንዴት?
በዘመናችን በክርስትና ስም ክርስቲያን ተብለው የሚጠሩ በጣም ብዙ ናቸው:: ክርስትና ማለትግን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተጠመቀ የክርስቶስ ተከታይ እና በክርስቶስ የሚያምን ማለት ነው ::
በክርስቶስ ማመንም፦
)የአብ የባህሪ ልጅ ነው ብሎ ማመን፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን የስም፣የአካል ሦስትነት አለው። በግብር ሶስትነት
አብ ወላዲ ነው ወልድን፤
ወልድ ተወላዲ ነው ከአብ የሚወለድ
መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ (ከአብ የወጣ) ነው፤
ይህ ማለት ግን አብ ወልድንና መንፈስ ቅዱስን በዘመን አይቀድማቸውም። በክብሩም አይበልጣቸውም። አብ አባት ስለሆነም አስቀድሞ በዮርዳኖስ በኋላም በደብረታቦር “ . . . በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጀ ይህ ነውአለ:: ማቴ ፲፯፦፭
)የባህሪ አምላክ ብሎ ማመን ማመን
ኢየሱስ ክርስቶስ የባህሪ አምላክ ነው (፩ኛ ዮሐ ፭፦፳ ) ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ክርስቶስ የባህሪ አምላክነት ሲገልጽፅ “ . . . ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነውብሏል:: ሮሜ ፱፦፭ አምላክነቱም የባህሪው ስለሆነ ለቅዱሳን የጸጋ (የስጦታ ) አምላክ ይሆን ዘንድ ይሰጣል(ይሾማል ) እንጂ እርሱ ከማንም አይቀበልም::
) እግዚአብሔር ነው ብሎ ማመን
የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ነው:: ይህንን እንደሚከተለው እንመለከታለን:: አስቀድሞ ኢዩኤል ነቢይ ” . . . የእግዚአብሔር ስም የሚጠሩ ይድናሉ”:: ብሎ ነበር :: ቅዱስ ጴጥሮስምየጌታ ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል:: “ ኢዩ ፸፦ ፴፪ የሐዋ :_፳፮ ብሎ ተናገረ :: ጌታ የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው :: ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ስለሆነ “. . . የእግዚአብሔር ስም የሚለውን የጌታ ስም ብሎ ደገመው “ :: እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ አረገ “ :: መዝ ፵፮(፵፯)፦፮ ይላል ነብየ እግዚአብሔር ዳዊት: : በእግዚአብሔር መውጣት መውረድ፡ መቀመጥ መነሳት የለበትም በአለም ምሉዕ (ምሉዕ በኩለኄ) ነውና : : የመድሀኒዓለም እርገት ሲነገር ነውና የሐዋ ፮፦፱
እግዚአብሔር ግልፅ ሆኖ ይመጣል የሚለውምእናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣልአላቸው መዝ ፵፬() የሐዋ ፩፦፲፩ ብለው የሚመጣ እግዚአብሔር እንደሆነ አስተምረዋል::
በመጀመሪያ ቃል ነበር ፡ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር :ቃልም እግዚአብሔር ነበር : ብሎ ወንጌላዊው ዮሐንስ የቃልን (የኢየሱስ ክርስቶስን ) እግዚአብሔርነት ጽፏል:: ኢሳ ፵፦፫ ማቴ ፫፦፫
) ፈጣሪ ነው ብሎ ማመን
ለፍጥረቱ መድሀኒት ለመሆን የፈጠረውን ሰው ከዳቢሎስ ቁራኝነት ከወደቀበት ለማንሳት የመጣ ኢየሱስ ክርስቶስ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ ነው:: ዩሐ ፩፦፫ መዝ ፴፪፦፮ ፈጣሪም ስለሆነ አማላጅ ሊሆን አይችልምና :: ምክናየቱም አማላጅ ሊሆን የሚችል ፍጡር ነውና ::
) ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በስልጣንና በህልውና አንድ መሆኑን ማመን
ስላሴ(አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ) በስልጣን በህልውና በባህሪ በፈቃድ ይህን ዓለም በማሳለፍ ይህን በመሳሰለው ነገር ሁሉ አንድ ናቸው:: (ዩሐ ፲፦፴ ዩሐ፲፬፦፲ )
) የተዋሀደው የድንግል ማርያምን ስጋና ነፍስ ነው ብሎ ማመን
አካላዊ ቃል ከሰማይ ስጋና ነፍስን ይዞ አልመጣም (አልወረደም) :: ሰው የሆነ ከድንግልማርያምስጋና ነፍስ ነስቶ በተዋህዶ ነው:: በመሆኑም እመቤታችን ቅድስት ድንግልማርያም ወላዲተ አምላክ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች ትባላለች::
) ትንሳኤውን ያለጥርጥር ማመን
ለድህነት ዓለም የመጣ እግዚአብሔር ሞትን በሞቱ ድል አድርጎ ተነሳ ሲነሳም በስጋ ነው:: ማቴ ፳፰፦፭ ሉቃ ፳፬፤፫ ፤ሉቃ ፳፬፤፴፮
) ያረገው በስጋው መሆኑን ማመን
መድሀኒዓለም ሞትን ድል አድርጎ በተነሳ በ፵ኛው ቀን እጁን በመጫን(በአንብሮተ እድ ) ሐዋርያትን እስከ ፓትሪያርክነት ሾሟል :: እርሱንም እያዩት የእርቀት ያይደለ (ከፍ ከፍ እያለ ) ከፍፁም ምስጋና ፈፅሞ ወደ አልተለየው ወደ ባህሪ አባቱ አርጓል::ያረገውም በስጋና በነፍስ፣በአጥንትና በደም፣በስጋና በጅማት እንዳለ ነው:: ፩ኛ ጴጥ ፫፦፳፭
) ሲመጣ በስጋ ማርያም መሆኑን ማመን
በኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ወቅት ለነበሩ ቤተሰቦች ቅዱሳን መላእክት እንደነገራቸውጌታችን ሲመጣ እየታየ በግልፅ ሆኖ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው (በተዋሃደው)ስጋ ነው :: መዝ ፵፱()፦፪ የሐዋ ፮፦፲፩ ራዕ ዮሐ ፮፦፯
እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነው መፅሀፍ ቅዱስ የሚነግረን ቅዱሳን አባቶቻችን የሚያስተምሩን ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ሳይሆን ተማላጅ፣ አንድ አካል አንድ ባህሪ፣ ፍጡር ሳይሆን ፈጣሪ እንደ ሆነ ነው:: የዘላለም ሀይወትን ለማግኘት እንግዲህ አምነን በመግባት ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ይገባናል::
ወስብሀት ለእግዚአብሔር


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ