ትምሕርተ ሃይማኖት/ክፍል ሁለት/
1 ሀልዎተ እግዚአብሔር/
ሀልዎት ፤ ሀለወ ኖረ ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ቃል ሲሆን ፤ የእግዚአብሔርን መኖር የምንረዳበት ትምሕርት ነው ።
በዚህ ትምሕርት ፤ . ስለ እግዚአብሔር ስሞች ።
. ስለ እግዚአብሔር ባህርይ ።
. እግዚአብሔርን ስለ ማየትና አለማየት ፤ የሚሉትን እናያለን ።
የእግዚአብሔር ስሞች እግዚአብሔር ራሱን ለሰዎች የገለጠው በስሙ ነው ። ዘፍ 12 ፥ 1 ። ዘፀ 3 ፥ 14 ። እኛ ሰዎችም እግዚአብሔርን የምናውቀው በስሙ ነው ። በስሙ እናምናለን ፤ ለስሙ እንሰግዳለን ፤ ስሙ ን ጠርተን እንድናለን ። በስሙ ለከበሩና ፡ ስሙ ለተጠራባቸው ፡(ቅዱሳን መላእክት ። ዘፍ 19 ፥ 1 ። ኢያ 5 ፥ 13 ። ቅዱሳን ሰዎች ፤ 1 ነገ 18 ፥ 7 ። ሮሜ 8 ፥ 30 ። የቤተ መቅደስ ንዋያት ። ዳን 5 ፥ 1 ። ቅዱሳት መካናት ። 2 ነገ 5 ፥ 17 ።) ተገቢውን ክብር እንሰጣለን ።
በምድራዊ አስተዳደር በአገር መሪነት ደረጃ ያሉ ሰዎች ፤ ስማቸው ፣ ቢሯቸው∙፣ ያላቸው ነገር ሁሉ የተከበረ ነው ። ጊዜያ ዊዉና የሚያልፈው በሌሎች ሰዎች የሚተካው ሥልጣን ይህን ያህል ከተከበረ ፡በዘመን የማይለካ ፣ በሌላ የማይተካ አምላክ ፤ ያከበራቸው ፣ የማያልፍና ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳኑን የሰጣቸው ፣ በስሙ የተጠሩ ቅዱሳንማ በብዙ ሊከበሩ ይገባቸዋል ። እኛ ቅዱሳንን ስናከብር የባህርይ አማልክት ናቸው ብለን ሳይሆን እግዚአብሔር በስሙ ስላከበራቸው እነሱን ማክበር አምላካቸውን ማክበር መሆኑን ስለምናውቅ ነው ። እኛ ሰዎች እንኳን የምንወደውን ሌላው እንዲወድልን እንፈጋለን ፡የማይሳሳተውና ፍጹም የሆነው አምላክ የወደዳቸውንና ያከበራቸውን ብናከብር ያከብረናል ።
የፍጡራን ስም የሚያገለግለው ለመለያነት ብቻ ነው ። ለምሳሌ ፀሀይ የሚባል ሰው ስሙ ለመጠሪያነት ከሚያገለግለው በቀር ፀሀይን ሊወክል አይችልም ። ሌላውም ስም ሁሉ እንዲሁ ተመሳሳይና ፡ አንዱን ከሌላው ለመለየት የሚያገለግል ነው ።
እግዚአብሔር ግን እንደ ስሙ ይሠራል ፡ነገር ግን ሁሉንም ባህርዩን የሚገልጽ አንድ ብቻ ስም የለውም ። ሁሉም ስሞቹ በየራሳቸው አንድን ሁኔታ ይገልጻሉ ።
ለምሳሌ ፤ እግዚአብሔር ።
1. ሀ. እግዚእ - ጌታ ብሔር - ዓለም = የዓለም ጌታ ። ጌትነቱን ይገልጻል ።
ለ. እግዚእ - ጌታ ወልድ
አብ - አባት አብ
ሔር - ቸር መንፈስ ቅዱስ
እግዚአብሔር የሚለው ቃል በአንድ ቃል ፡ሲገለጥ የዓለም፡ጌታ.ገዥ ማለት ነው ።
በተጨማሪም ፡እግዚአብሔር » የሚለው ስም ፡እግዚአብሔር አብ ፣ እግዚአብሔር ወልድ ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፤ በማለት(የሥላሴ) የሶስትነቱን ስም ይገልጻሉ ።
2. ኢየሱስ ፤ ማለት መድኃኒት ማለት ነው ፡ እሱ ሞቶ ሕይወቱን በመስጠት ዓለምን ያዳነ::
3. ክርስቶስ ፤ መሲህ ፣ መንግሥቱ የማያልፍ እውነተኛ ንጉሥ ማለት ነው ።
4. አማኑኤል ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው ። ይህም፡ማለት ፡ አምላክ መለኮታዊ ባህርዩን ከሰው ባህርይ ጋር በማዋሃድ ፡ ፍጹም አምላክነቱን ፡ሳይለቅ ፡ ፍጹም ሰው ሆነ ማለት ፡ ነው ።
5. መድኃኔ ዓለም ፤ የዓለም መድኃኒት ። ይህ ቃል ግዕዝ ሆኖ ኢየሱስ ከሚ ለው ጋር የትርጉም አንድነት አለው ።
6 ኤል ፤ ኃያል አምላክ ማለት ነው ። በዚህ ዓለም ያለው የአንዱ ኃይል ከሌላው ኃይል ይበልጣል ፡የሁሉም ኃይል በመጠን ይለካል ። የእግዚአብሔር ግን ኃይሉ የማይመጠን ፣ የኃይለኞች ኃያል ፣ የብርቱዎች ብርቱ ፣ በተናቁት ወዳጆቹ አድሮ ኃይል በመስጠት ፡ ታላቅ ሥራን የሚሠራ ፤ ኃያል አምላክ ነው ።
ሌሎችም ክብሩንና ሁሉን አድራጊነቱን የሚገልጹ ስሞች አሉት ። ይሁን እንጂ የእግዚአብሔርን ባህርይና ከሀሊነት… ሙሉ ፡በሙሉ፡በሰው፡ቃላት መግለጽም ሆነ ማስረዳት ፡አይቻልም ምክንያቱም ፍጹም የሆነውን የአምላክ ባህርይ የሰዎች ውሱን አእምሮ ሊደርስበትና፡ሊወስነው አይችልምና ። ነገር ፡ግን በእርሱ ፡አምነን ፡የዘለዓለም ፡ሕይወት እናገኝ ዘንድ እኛ ሰዎች በምንረዳው አቅም ራሱን ገለጠልን ።
ቅዱሳን መላእክትና ቅዱሳን ሰዎች ፤ ስማቸውን ፤ «ኤል» ከሚለው የእግዚአብሔር ስም ጋር እያጣመሩ በመጠራት የአምላክ አገልጋዮችና ስጦታዎች እንዲሁም የኃይሉ መገለጫዎች መሆናቸውን ገልጸውበታል ።
ከነዚህም መካከል ፤ የሚከተሉትን እናያለን ።
ስም
ሚካኤል ፤ (መኑ ከማከ) ማን እንደ አምላክ ማለት ሲሆን ። ሰያሜውም የአምላክ፡ ባለሟልነቱን ይገልዓል
ገብርኤል ፤ ገብር አገልጋይ = የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ሲሆን የሁሉም መላእክት ስማቸው ኤል ከሚለው የእግዚአብሔር ስም ጋር የተጣመረና ትርጉሙም ተግባራቸውን የሚገልጽ ነው ።
ከሰዎች መካከልም « ኤል » ከሚለው የእግዚአብሔር ስም ጋር ተጣምሮ የሚጠራ ስም የጥቂቶችን እንደሚከተለው እናያለን ።
ሳሙኤል ፤ ሳሙ - ስም ኤል - አምላክ = የእግዚአብሔር ስም ።
ኤልያስ ፤ ኤል - አምላክ ያስ - አምላክ = እግዚአብሔር አምላክ ነው ።
ዳንኤል ፤ ዳን - ዳኛ ኤል - አምላክ = እግዚአብሔር ዳኛ ነው ።
ሕዝቅኤል ፤ ሕዝቅ - ብርታት ኤል - አምላክ = እግዚአብሔር ብርታት ነው ።
ኢዩኤል ፤ ኢዩ - አምላክ ኤል - አምላክ = እግዚአብሔር አምላክ ነው ።
ናትና ኤል ፤ ናትና - ስጦታ ኤል - አምላክ = የእግዚአብሔር ስጦታ ።
2 የእግዚአብሔር ባህርይ
የእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህርይ በሰው አእምሮ የማይመረመርና የማይወሰን ረቂቅ ነው ። በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር መመራመርም ሆነ ለሌላውም ማስረዳት ይቻላል ።
የመለኮትን ባህርይ ግን ሙሉ በሙሉ ተመራምሮ የሚያውቅም ሆነ የሚያስረዳ ማንም የለም ። ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት በገለጹልን መሠረት እንደሚከተለው ለመግለጽ እንሞክራለን ።
2.1 እግዚአብሔር መንፈስ (ረቂቅ) ነው
እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእምነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል ። ዮሐ 4 ፥ 24 ። በማለት ጌታችን እንደተናገረ እግዚአብሔርን ስናምን በዓይናችን አይተን ፣ በእጃችን ዳስሰን አረጋግጠን ሳይሆን በመለኮታዊ ባህርዩ በሥጋ ዓይን የማይታይ አምላክ መሆኑን አምነን በመቀበል ነው ። እግዚአብሔር መንፈስ ነው ስንልም ። በእኛ አእምሮ የማ ይታወቅ ፤ መጠን የማይሰጠው ፤ በላብራቶሪ ምርመራ የማይደረስበት ፤ ከምርምር ውጭ የሆነ አምላክ ማለታችን ነው ።
እግዚአብሔር የፈጠረው ነፋስን እንኳን ከረቂቅነቱ የተነሳ በዓይናችን ማየት እንደማንችል ሁሉ ። ዮሐ 3 ፥ 8 ። ረቂቃን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ መለኮታዊ ባህርዩ ሊመረመርና ሊገመት የማይችል ረቂቅ ነው ።
2.2 እግዚአብሔር በሁሉም ሙሉ ነው
ሰው በአንድ ጊዜ በሁሉም ቦታ መገኘት የማይችል በተወሰነ ቦታ ብቻ የሚወሰን ነው ። ኤር 23 ፥ 23 ። እግዚአብሔር ግን ፍጡር የማይወስነው ፣ በሁሉም ቦታ የሚገኝ ፣ (ምሉዕ በኩለሄ የሆነ) አምላክ ነው ። እግዚአብሔር በዓለም ሙሉ ነው ሲባል በዓለም ውስጥ ብቻ ተወስኖ ይኖራል ማለት ሳይሆን ዓለምን በውስጡ ይወስናል ማለት ነው ። በኢሳ 8 ፥ 1 ። “ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት ።” የሚለው ቃል እግዚአብሔር በዚህ አካባቢ ብቻ አለ ተብሎ ቦታ የማይወሰንበት ፡ ሰማይም ምድርም ዓለማት በሙሉ ግዛቱ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነው ።
2.3 እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው
ሰዎች በዚህ ዓለም መኖር የሚችሉት በሕይወት እስካሉ ድረስ ብቻ ነው ። ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊ ኑሯቸው በሞት ይለወ ጣል ። ዘፍ 3 ፥ 19 ። እግዚአብሔር ግን ዓለማት ሳይፈጠሩ የነበረ ፣ አሁንም እየገዛ ያለ ፣ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚ ኖር ፣ በባህርዩ ሞት ፣ በመንግሥቱ ሽረት የሌለበት ዘለዓለማዊ አምላክ ነው ።
እኛ ሰዎች የተወለድንበት ቀን መጀመሪያችን ፤ የምንሞትበት ቀን መጨረሻችን ነው ፤ አምላክ ግን ሰው በመሆኑ ዘመን ቢቆ ጠርለትም ፤ ሥጋ ፡ የመለኮትን ባህርይ በተዋሕዶ ገንዘቡ ስላደረገ “ስለተዋሃደ” ፤ ዘመናት የማይቀድሙት ቀዳማዊ ዘመናትን አሳልፎ የሚኖር ደኃራዊ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘለዓለማዊ አምላክ ነው ። ራዕ 1 ፥ ፲፰ ለነበረበት መጀመሪያ ፤ የማይኖርበት መጨረሻ የለውም ፤ ለሁም ነገር መጀመሪያውም ሆነ መጨረሻው ራሱ ነው ። ዘፍ 18 ፥ 14 ዘፀ 3 ፥ 14 ።
2.4 እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ነው
እኛ ሰዎች በሕይወት ዘመናችን ማድረግ ወይም ማግኘት የምንችለው የተወሰነ ነገር ብቻ ነው ።
ለምሳሌ ፤ በዓለም ያለውን ዕውቀት ፣ ሀብት ፣ ሥልጣን፣.. ሁሉ በአንድ ጊዜ ማግኘት አንችልም ። ብዙዎቻችንም «ያለኝ ይበ ቃኛል» ብለን በተሰጠን ከማመስገን ይልቅ ሌላውን ሆነን ለመገኘት የምናደርገው ድካም በእኛነታችን ውስጥ ጉድለት እንዳለና ሁሉንም ማድረግም ሆነ መሆን እንደማንችል ያስረዳል ። እግዚአብሔር ግን ያለማንም እርዳታ በማንኛውም ሰዐት የወደ ደውን ማድረግ የሚችል ፣ ጌትነቱ ፣ ዕውቀቱ ፣ ሀብቱ ፣ የራሱ የሆነ ፤ ከማንም ምንም የማይሻ ፤ ሁሉ ያለው ፤ የማይደክም ፣ የማይሰለች ፣ የሚሳነው ነገር የሌለ አምላክ ነው ። ዘፍ 18 ፥ 13 ። ሉቃ 1 ፥ 37 ። ኢሳ 40 ፥ 2 ።
2.5 እግዚአብሔር ጥበበኛ (አዋቂ) ነው
የሰው ልጅ ይዞት የተወለደው ልቅሶ ብቻ ነው ። ሌላውን ሁሉ ፡ በማየት፣ በመስማት ፣ በመማር ፤ ከሰዎች ያገኘው ነው ። ያውም ቢሆን ያለፈውን ታሪክ ከማውራትና አሁን የሚደረገውን ከማየት በቀር ወደ ፊት የሚሆነውን ለማወቅ የሚያስችል ዕው ቀትና ጥበብ የለውም ። ዕውቀቱም ቢሆን የአንዱ ዕውቀት ከሌላው ይበልጣል ፤ በዚህ ዓለም ፍፁም የሆነ ዕውቀት የለም የተከፈለውም ቢሆን በጊዜው ያልፋል ። 1ቆሮ 13 ፥ 8 ። እግዚአብሔር ጥበቡ የባህርዩ የሆነ ፣ ያለፈውን የማይረሳ ፣ የሚያውቅ ፣ ለሰዎች ዕውቀትንና ጥበብን የሚገልጽ አምላክ ነው ። ሰው ሊያውቅና ሊመራመር የሚችለው ውጫዊውንና ግዙፉን ነገር ብቻ ነው ። እግዚአብሔር ግን ልብና ኩላሊትን (በሰው ህሊና የታሰበውን) አስቀድሞ የሚያውቅ አምላክ ነው ። መዝ 7 ፥ 9 ።
2.6 እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
ቅድስና የእግዚአብሔር የባህርዩ ሲሆን “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ዘሌዋ 19 ፥ 2 ። 1 ዼጥ 1 ፥ 15 ። ባለው ቃል መሠረት ቅዱሳን መላእክትና በሥራቸው ለቅድስና የበቁ ሰዎችም ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ ።
የመላእክትና የሰዎች ቅድስና ግን ፡ በሥራ የሚገኝ ፣ በሃይማኖት የተፈተነ ፣ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ የፀጋ ቅድስና ነው ። የፍጡራን ቅድስና ፡ደረጃ አለው ከአንዱ የሌላው ይበልጣል ። 1 ቆሮ 15 ፥ 41 ። የእግዚአብሔር ቅድስና በመጠን አይወሰንም ፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለምና ። ኢሳ 6 ፥ 3 ። ዕንባ 1 ፥ 13 ።
2.7 እግዚአብሔር ቸር ነው
የሰው ልጅ ቸርነቱ (ልግስናው) በኪሱ ያለው ሳንቲም እስኪያልቅ ፤ እሱንም ቢሆን የሚሰጠው ተለምኖ ነው ። እግዚአብ ሔር
ሁሉ ያለው ፣ ያለ ንፍገትና ያለ መሰሰት ለጋስ ፣ ስጦታው የማያልቅበት ፣ ኃጥዕ ጻድቅ ሳይል በቸርነቱ ለሁሉ ያለ አድልዎ የሚያድል ማቴ 5 ፥ 41 ። ሳንለምነው የሚያስፈልገንን አውቆ የሚሰጠን ፣ ቸር አምላክ ነው ። ማቴ 6 32 ። ሰው የሚሰጠው ከሌላው ያገኘውን ነው ፤ ወደዚህ ዓለም የመጣው ራቁቱን ነው ፤ ወደ ምድር ሲመለስም የሚያስከትለው ነገር የለውም ። ኢዮ 1 ፥ 21 ። 1ጢሞ 6 ፥ 7 ። እኛ ለሌሌሎች የምንሰጠው ከተረፈን ብቻ ነው አምላካችን ግን ለእኛ የሰጠን ራሱን ነው ። ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም ። ዮሐ 15 ፥ 13 ። ሰው የሚሰጠው ለወዳጁ ፣ ለወገኑ ፣ ለሚመስለው… ነው እግዚአብሔር ግን ጠላቶቹ ሳለን ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ከራሱ ጋር አስታረቀን ፤ ከዘለዓለም ሞትም አዳነን ። ሮሜ 5 ፥ 10 ።
2.8 እግዚአብሔር ፍቅር ነው
ሰው ወዳጁን ይወዳል ለማይወደው ግን ቦታ አይሰጥም ፤ እንዲያውም ከተመቸው ከመበቀል ወደኋላ አይልም ። እግዚአብ ሔር ግን እየበደልነው ለንስሐ እስክንዘጋጅ በብዙ ታግሶ ይወደናል ። ሮሜ 2 ፥ 4 ። የሰው ፍቅሩ ተለዋዋጭ ፣ ወረት ያለበት ፣ ጊዜያዊ ነው ። ሰው ለጥቅም ብሎ ወዳጁን ይገድላል ። አምላካችን ፍቅሩ የማይለካ ፣ ለእኛ ለጠላቶቹ የሞተ ፤ ኢሳ 53 ፥ 1 ፥12 ። የሠራነውን ሁሉ በቸርነቱ ይቅር ብሎ ከበደል የሚያነጻን አምላክ ነው ። ኢሳ 1 ፥ 18 ። እግዚአብሔር ፈቅደን እንድንገዛለት ይፈልጋል እንጅ ፤ ማንኛችንንም አስጨንቆ አይገዛንም ። 1 ዮሐ 1 ፥ 8 ።
2.9 እግዚአብሔር በእውነት የሚፈርድ እውነተኛ ዳኛ (ፈራጅ) ነው
እግዚአብሔር ለሰዎች የዳኝነት ሥልጣን የሰጣቸው ትክክለኛ ፍርድ እንዲፈረዱ ነው ። ማንም ቢሆን እውነት መፍረድ እንዳለበት ህሊናው ይነግረዋል ። በሐሰት ስንፈርድ በመጀመሪያ የሚወቅሰን ህሊናችን ነው ። የህሊና ወቀሳን የማይፈራ ማንንም ሊፈራ አይችልም ። ዳኞች ፡ በዘመድ ፣ በጥቅማ ጥቅም ፣ በዓላማ መመሳሰል ፡ እና በሌላም ፍርድ ሊያዛቡ ይችላሉ ። እግዚአብሔር ግን ከማንም ምንም የማይፈልግ ፣ ከእውነት ጋር ደስ የሚለው ፣ ፍርዱ ትክክለኛ የሆነ አምላክ ነው ። እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያደላም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል ። ራዕ 22 ፥ 12 ። መዝ 36 ፥ 28 ።
3. እግዚአብሔርን ስለ ማየትና አለማየት
3.1 የእግዚአብሔርን መኖር የምናረጋግጠባቸው ነገሮች
በዓለማችን ያሉት ነገሮች ሁሉ የአምላክን መኖር የሚገልጹ ቢሆኑም የተወሰኑትን በማስረጃነት እናያለን ። አንድን ሰው ዘመ ናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን ተጠቅመን ድምፁን በመስማት ወይም በአካል በማየት መኖሩን መረዳት እንችላለን ። የእግዚአብሔርን መኖር የምናውቅባቸው መንገዶች ግን ከዚህ የተለዩና በሚከተሉት መንገዶች የሚገለጹ ናቸው ።
3.2 ሥነ ፍጥረት
“ራሱን ያለ ምስክር አልተወም” ። የሐ ሥ 14 ፥ 17 ። በአንድ ባለሙያ (በፋብሪካ) የተሰሩ ነገሮች ሰሪያቸውን እንደሚያስተዋውቁና እንደሚያስመሰግኑ ሁሉ ፍጠረታትም በእርሱ እንደተፈጠሩና እንደሚመሩ ስለ እግዚአብሔር መኖር ምስክሮች በመሆን ፈጣሪያቸውን ያስተዋውቃሉ #
“የማይታይ እግዚአብሔር በፍጥረቱ ይታወቃል” ። ሮሜ 1 ፥ 20 ። ባለሞያ በሰራቸው ስራዎች እንደሚታወቅ ሁሉ እግዚአብሔርም በፈጠራቸው ፍጥረታት ይታወቃል ። በምድራችን በራሱ የተገኘ ምንም ነገር የለም ፡ ሁሉንም ነገሮች የፈጠረ እግዚአብ ሔር ነው ።መዝ 23 ፥ 1 ። ሰዎች ለሚሰሯቸው ስራዎች በዲዛይንነት የሚጠቀሙት የአምላክ ስራ የሆኑ ፍጥረታትን ነው ። የሰዎች ሥራ ፋሸኑ ያልፋል በሌላ ስልጣኔ ይተካል ። የአምላክ ስራ ግን የማይጠገብ ፡የማይሰለች ፡ ሁሌም አዲስ ነው ። ፍጥረታት እግዚአብሔር እንደፈጠራቸው በዝምታ ይናገራሉ ይመሰክራሉም ። ኢዮብ 12 ፡7-9 ። መዝ 18 ፥1 ።
3.3 የሰዎች ህሊና ምስክርነት
የሰዎች ህሊና ስለ እግዚአብሔር መኖር ምስክር ነው ። ክፉ ሲሰራ ይፀፀታል " መልካም በሚሰራበት ወቅት ደግሞ ደስተኛ ይሆናል ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎችም ቢሆኑ በህሊናቸው አውቀው ጥፋተኛው የሚቀጣበትን ህግ ያወጣሉ ። ሮሜ 2 ፥ 19 ። ሰዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ነገር “እሱ ያውቃል” በማለት ለእግዚአብሔር ይሰጣሉ ። ምንም እንኳን ክፉ ቢሰሩ ለሁሉም እንደስራው የሚከፍል አምላክ እንዳለ በህሊናቸው ያምናሉ ፡ ሰው አምላኩን ይመስላል የተባለውም በመልካም አስተሳሰቡ (ህሊናው) ነው ።
3.4 የታሪክ ምስክርነት
ታሪክ ያለፈውንና እውነት የሆነውን ነገር ለአዲሱ ትውልድ የሚያስረዳ ሲሆን ፤ በዓለም ላይ የተፈፀሙና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ታሪኮች ስለ እግዚአብሔር መኖር ግልጽ ምስክርነት ይሰጣሉ ።
ለምሳሌ እስራኤል በግብፅ አገር ለ430 ዓመታት መኖራቸው በታሪክ ተመዝግቧል ። ይህ ታሪካዊ ድርጊትም የተፈጸመው በእ ግዚአበሔር ጥበብ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል ። ዮሴፍ በመጀመሪያ ወደ ግብፅ ወርዶ ባለስልጣን በመሆን ለወገኖቹ ከሀገራቸው መፍለስና ለጊዜውም ቢሆን የተሻለ ሕይወት ይኖሩ ዘንድ ምክንያት እንዲሆን ያደረገና ዘፍ 41 ፥ 39 ።
ሙ ሴ በአስቸጋሪ ወቅት በአስደናቂ ሁኔታ ተወልዶ በቤተ መንግስት እንዲያድግና በኋላም እስራኤልን እየመራ ከግብፅ ወደ ከነዓን እንዲያወጣ ያደረገ እግዚአብሔር ነው ። ዘፀ 3 ፥ 1 ። ሌሎችም በዓለም ታላላቅ የተባሉ ታሪኮችን በማስተዋል ከተረዳና ቸው የእግዚአብሔር ኃያልነትና ሁሉን አድራጊነት እንደተገለፀባቸው ማወቅ እንችላለን ።
በሌላም በኩል በዓለም ታሪከ ትልቅ ቦታ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ስለ እግዚአብሔር መኖርና ስለ ድንቅ ስራዎቹ እንዲሁም በወዳጆቹ ላይ አድሮ ያደረጋቸው ተአምራትና መለኮታዊ ኃይሉን ነው ። በተጨማሪም የእግዚአብሔር ስም የተጠራባቸው “ፀበሉ ፤ እምነቱ ፤ መስቀሉ….ተአምራት ሲያደርጉ ፤ ህሙማን የእግዚአብሐርን ስም ጠርተው ፤ መዳናቸው እውነተኛና ህያው ምስክር ናቸው ። በማስተዋል ለሚ ገነዘበው በዓለም ላይ የእግዚአብሔር ኃይል ያልተገለጠበት የታሪክ ክፍል የለም ።
3.5 እግዚአብሔርን የማናይበት ምክንያት ።
በእርግጥ እግዚአብሔር ለአብርሐም በ፫ ሰዎች አምሳል ። ዘፍ 18 ፥ 1 ለኢሳይያስ በንጉሥ አምሳል ። ኢሳ 6 ፥ 1 ። ለሌሎችም ወዳጆቹ በተለያየ መንገድ ቢገለጽላቸውም እሱ በወደደውና እነሱ ማየት በሚችሉት መጠን እንጅ እግዚአብሔርን በመለኮታዊ ባህርዩ ያየው ማንም የለም ። ዘፀ 33 ፥ 20 ። ዮሐ 1 ፡18 ። ማቴ 17 ፥ 6 ።
4 እግዚአብሔርን በዓይናችን የማናይባቸው ምክንያቶች
1. ስለ ታላቅነቱ
2. ስለ ብርሃናዊነቱ (አንፀባራቂነቱ)
3. ስለ እሳትነቱ (አቅላጭነቱ)
4. ስለ ረቂቅነቱ
5. ስለ ድምፁ አስፈሪነት…. ነው ።
4.1 የአግዚአብሔር ታላቅነት
በዚህ ዓለም ያሉ ፍጥረታት መጠናቸው ከአንዱ የሌላው ያንሳል ወይም ይበልጣል ። እያንዳንዳቸውም መለኪያ አላቸው ። ስለ እግዚአብሔር ታላቅነት ስንማር ግን ይህን የዓለም ቀመር ከህሊናችን ማውጣት አለብን ። ምክንያቱም የእግዚአብሔር የሆነን ነገር ሰው በሥጋዊ ዕውቀቱ ተመራምሮ ሊደርስበት አይችልምና ። ነቢዩ “ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት” ። ኢሳ 66 ፥ 1 ። በማለት የተናገረው በሰማይና በምድር ብቻ ይወሰናል ለማለት ሳይሆን ሰማይም ምድርም በእኔ ግዛት ውስጥ ናቸው ፤ እኔ በሁሉም እገኛለሁ ፤ ፍጥረታትን እኔ እወስናቸዋለሁ እንጅ እነሱ አይወስኑኝም ለማለት ነው ። እኛ ሰዎች በአምላክነቱ ውስጥ ያለችውን ዓለም እንኳን በአንድ ጊዜ ማየት አንችልም ። እግዚአብሔርን የማ ናየው ፤ ዓለማትን የሚወስንና ከምናስበው በላይ በእጅጉ ታላቅ በመሆኑ ነው ።
4.2 የእግዚአብሔር ብርሃናዊነት (አንፀባራቂነት)
ሰው ማየት የሚችለው የብርሃን መጠን ማየት በሚችለው ልክ ከሆነ ብቻ ነው ። ከዚያ ከበዛም ሆነ ካነሰ ማየት አይችልም ።
ለምሳሌ የፀሀይን ብርሃን ወይም ሌላ ከፍተኛ የብርሃን ነፀብራቅ ሙሉ በሙሉ በዓይን ማየት አይቻልም ። ዘፀ 34 ፥ 27 ። ሙሴም እንኳ 40 ቀንና 40 ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር በሲና ተራራ ቆይቶ ከተመለሰ በኃላ የፊቱ ብርሃን ስለ አንፀባረቀባቸው እስራኤል ማየት አልቻሉም ነበር ። የሰው ልጅ ፤ ለፍጡራንን በፀጋ የተሰጠ የብርሃን ነፀብራቅን ተቋቁሞ ማየት ከልተቻለ የፈጣሪውን መለኮታዊ ብርሃን የማየት አቅም እንደየት፡ሊኖረው፡ይችላል፡? ማቴ 17 ፡ ፥ 6 ።
4.3 የእግዚአብሔር እሳትነት (አቅላጭነት)
በተፈጥሯቸው ከፍተኛ የሆነ የሙቀት (አቅላጭነት) ባህርይ ባላቸው ነገሮች አካባቢ ለመኖር እንደማይቻል ይታወቃል ።
ለምሳሌ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ፤ ከፍተኛ የሙቀት አየር ያለበት አካባቢ መኖር አይቻልም እነዚህ ፍጡራን ሲሆኑ ይህን ያህል የማቃጠል ኃይል ካላቸው ፤ እነዚህን የፈጠረ አምላክማ መለኮታዊ ባህርዩ ከምናስበው በላይ አቅላጭ (እሳትነት ያለው) በመሆኑ ሰው አይቶት በፊቱ መቆም አይችልም ። ዘፀ 33 ፥ 20 ።
4.4 የእግዚአብሔር ረቂቅነት
ነፋስ (አየር) ረቂቅ ነው ። ድምፁን እንሰማለን ከየት እንደሚመጣ ወዴትም እንደሚሄድ ግን አናውቅም ሌሎችም በዓይናችን የማናያቸው ብዙ ረቂቃን ነገሮች አሉ ከነፋስ ነፍስ ፤ ከነፍስ መላእክት ይረቃሉ ። እነዚህ ረቂቃን በመሆናቸው ማየት ካልቻልን ሁሉንም የፈጠረ አምላክ ፤ መለኮታዊ ባህርዩ ማሰብና መገመት ከምንችለው በላይ ረቂቅ በመሆኑ በዓይናችን ልናየው አንች ልም እግዚአብሔር መንፈስ ነው ፤ የሚሰግዱለትም አይተው ሳይሆን ፤ በመንፈስ ይሰግዱለታል ተብሏልና ። ዮሐ 4 ፥ 24 ።
4.5 የእግዚአብሔር የድምፁ አስፈሪነት
ጆሯችን መስማት የሚችለው የድምፅ መጠን አለው ፤ ከአቅሙ በላይ ድምፅ ከሰማ የጤና መታወክ ሊደርስበት ይችላል ። አንዳንድ ጊዜ መስማት ከምንችለው በላይ የሆኑ ድምፆች ሲያጋጠሙን ጀራችንን በእጃችን በመድፈን እንከላከላለን በዓለማ ችን መስማት ከምንችላቸው በላይ የሆኑ ብዙ ድምፆች አሉ ።
እስራኤል የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት ከመፍራታቸው የተነሳ ፤ ሙሴን “እንዳንሞት እግዚአብሔር አይናገረን አንተ ተናገረን” ይሉት ነበር ። ዘፀ 20 ፥ 19 ። በሌላም በኩል አይሑድ ጌታን ሊይዙ በመጡበት ሰዓት “የናዝሬቱ ኢየሱስ እኔ ነኝ” ባላቸው ጊዜ ቁመው መስማት ስላልቻሉ መሬት ላይ ወደቁ ። ዮሐ 18 ፥ 4 ። አምላክ በሥጋ በተገለጠበትም ሆነ በሌላ ጊዜ ሰዎችን የሚያነጋግራቸው መስማት በሚችሉት መጠን እንጅ መለኮታዊ ድምፁን ሰምቶ በህይወት መኖር የሚችል ማንም ፍጡር የለም ።
ከላይ የገለጽናቸው ሁሉ የእግዚአብሔር ባህርይ በሰው አእምሮ የማይወሰንና በምርምር የማይደረስበት መሆኑን ለማስረዳት ያህል እንጅ አምላክነቱን በሙሉ ያስረዳሉ ማለት አይደለም :: የእግዚአብሔርን ይቅርና የሰውን ባህርይ እንኳን ማወቅ ይከብ ዳል ይሁን እንጅ የእኛን ታናሸነትና ውሱንነት ፤ የእግዚአብሔርን ኃያልነት ለመረዳትና ለማወቅ ይረዳ ዘንድ ይህ ተጻፈ ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ