ሰኞ 2 ማርች 2015

‹‹ከእኔ አብ ይበልጣል›› ዮሐ 14፡28 የይሆዋ ምስክሮች እብደት ክፍል አንድ
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋእለ ስጋዌው /ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በሚመላለስበት ጊዜ/ ወደ አብ መሄጃ ጊዜው በመድረሱ ደቀመዛሙርቱን ሰብስቦ ወደአብ መሄዴ ነው በመሄዴ አትዘኑ አትከፉ አብ ከኔ ይበልጣል ብሎ የተናገረውን ቃል በመያዝ አንዳንድ መናፍቃን እና አህዛብ ኢየሱስ አብ ከእኔ ይበልጣል ስላለ ከአብ ያንሳል ፍጡር ነው እያሉ ሲናገሩ በቃሉ ሲሰናገሉ እንመለከታለን ፡፡እውነት እነርሱ እንደሚሉት ኢየሱስ ከአብ ያንሳል እስቲ የጥቅሱን የመልእክቱን ፍሬ ነገር አብረን እንመልከት፡፡
ጌታ ኢየሱስ ይህንን ያለበት ምክንያት ስጋን በመልበሱ ህማም ሞት ግርፋት ስቃይ የመስቀል መከራ ስለሚደርስበት ነው ፡፡ አብ ግን ስጋን ስላለበሰ ህማም ሞት መከራ ስቃይ አያውቀውም /አይደርስበትም/ የለበትም በዚህ ምክንያት አብ ከኔ ይበልጣል በዚህ ሰአት እኔ ወደመከራ ግርፋት ስቃይ መሄዴ ነው ወደ አባቴ መሄዴ መልካም ነው እሱ ዘንድ መከራ የለም ግርፋት የለም ስቃይ የለም ስጋን በመልበሴ በሚደርስብኝ መከራ ምክንያት አብ ከኔ ይበልጣል አለ፡፡
ጌታችን ስጋን በመዋሀዱ ምክንያት እንኳን ከአብ ከመላእክትም አንሶ እንደነበር ቅዱስ ጳውሎስ በእብራውያን መልእክቱ ይነግረናል ዕብ 2፡9‹‹ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን።›› መላእክት ስጋን ባለመልበሳቸው/ሰው ባለመሆናቸው/የሚደርስባቸው መከራ እና ስቃይ ባለመኖሩ የመላእክት ፈጣሪ ከመላእክት አንሶ ነበር ተብሎ ተፃፈ ፡፡
ስናጠቃልለው ኢየሱስ ራሱን ባዶ አድርጎ ‹‹በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ዝቅ አደረገ፡፡›› ፊልጵስዩስ 2፡6 ስጋ ለብሶ/ፍፁም ሰው ሆኖ/ ወደዚህ ምድር በመምጣቱ በሚደርስበት መከራ ስቃይ ሞት የተነሳ እንኳን ከአባቱ ከመላእክትም አንሶ እንደነበረ ነገር ግን ከአባቱ ጋር አንድ እንደሆነ/በስልጣን በአገዛዝ ይህንን አለም በመፍጠሩ……………./ መላእክትንም የፈጠረ እርሱ እንደሆነና ከመላእክት አብዝቶ እንደሚበልጥ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠ እውነት ነው፡፡ዮሐ 10፡29 -34 ፤ ዮሐ 5፡18 ፤ዪሐ1፡1-14

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ