‹‹እግዚአብሔር መንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ›› ምሳ 8፡22 /የጂሖቫውያን ቅዠት ክፍል ሁለት/
በመጀመሪያ ክፍል ‹‹ከእኔ አብ ይበልጣል ››የሚለውን ጥቅስ አንስተን መልስ እንደሰጠንበት ይታወሳል ቀጣዩን እነሆ
‹‹መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል
አታውቁምና ትስታላችሁ› ማቴ 22፡29 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን
ሀይለቃል የተናገረው ፈሪሳውያን እና ሰዶቃውያን ወደ እርሱ ቀርበው ስለትንስኤ ሙታን ጥያቄ ጠይቀውት መልስ ቢሰጣቸውም ስላልተረዱ
/አረዳዳቸው መልእክቱን በማጣመም ስለሆነ/ ሲስቱ በመመልከቱ ነው፡፡አሁን በዘመናችንም በክርስትና ስም የተመሰረቱ ድርጅቶች መፅሐፍ
ቅዱስን ባለመረዳት የእግዚአብሔርንም ሀይል ባለማወቅ ሲስቱ እና ሲያስቱ ይታያሉ ለዛሬ ራሳቸውን የይሖዋ ምስክሮች ብለው ስለሰየሙ
ፍጹም ከክርስትና መሰረተ እምነት ውጭ ሁነው በአደገኛ ሁኔታ ስለሚንቀሳቀሱ አርዮሳውን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዙሪያ የሚያነሱትን
ጥያቄ የእግዚአብሔርን ቅዱስ መንፈስ አጋዥ አድርገን እንማማራለን እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ማንነት በቤተክርስቲያን አስተምህሮ
ቅድስት ሐዋርያዊት እና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን
መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርጋ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት አሉት ብላ ታምናለች ፡፡ይህም፤-
1.ቅድመአለም ያለእናት ከአብ ተወለደ መዝ 2፡7
፤ መዝ 109(110)፡3 ፤ ማቴ 3፡17 ፤ ዕብ 1፡5 ፡ምሳ 8፡22
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ
ያለእናት ከእግዚአብሔር አብ ተወለደ ይህ ሲባል እንደሰው ተፈጥሮ አስቀድሞ እናት እና አባት ተፈጥረው ልጅ እንደሚወልዱት አይነት
መራባት አይደለም አይደለም አባት ልጁን እንደሚቀድመው መቀዳደም በሁለቱ
የለም አስቀድሞ አብ ነበር ቀጥሎ ወልድ ተወለደ/መጣ/ ማለትም አይደለም ወልድ/ኢየሱስ/ ያልነበረበት ጊዜ የለም እርሱ መጀመሪያ
የሌለው መጀመሪያ ነው መጨረሻ የሌለው መጨረሻ ነው፤ ከእውነተኛ አምላክ
ተገኘ እውነተኛ አምላክ ከብርሀን የተገኘ ብርሀን ነው፡፡አብ ወልድን ወለደ ሲባል በመልክ የሚመስለው በባህሪ የሚተካከለው ልጁ ነው
ማለት ነው፡፡ የሰው ልጅ ሰው እንደሚባል ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ይባላል፡፡
2.ድህረ አለም/5500 ዘመን ሲፈፀም/ ያለአባት
ከድንግል ማርያም ተወለደ ኢሳ 7፡14 ፤ ኢሳ 9፡6 ፤ ሉቃ 2፡11 ፤ ገላ 4፡4
ይህም ሲባል ለአዳም በገባው ቃልኪዳን መሰረት
ከዳዊት ወገን ከሆነች ንጽህይት ቅድስት ድንግል ማርያም ያለአባት በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፍፁም ሰው ሁኖ ያለዘር ያለእሩካቤ በአምላክ
ፈቃድ ተወለደ ፡፡ ፍጹም ሰው በመሆኑ እንደሰው ይበላል ይጠጣል ይደክማል ይራባል ይጠማል አምላኬ ይላል ይፀልያል…………..ሰው የሚሰራውን ስራ ከሀጢያት በቀር ፈጽሟል፡፡ስለዚህም የሰው
ልጅ ተብሎ ይጠራል፡፡
ማሳሰቢያ ፡-ወደፊት እግዚአብሔር ቢፈቅድ ተዋህዶ
በሚል ርእስ በሰፊው እንማማራለን
ከላይ እንደተመለከትነው ቤተክርስቲያን መጽሐፍ
ቅዱስን መሰረት አድርጋ እምነቷ መሰረት የሆነውን ጌታ ኢየሱስን ወልድ ዋህድ ብላ ትጠራዋለች ታምነዋለች ትሰብከዋለች ህም ቤተክርስቲያን
የእምነት መሰረት ነው ይህን የማያምን ፍፁም ክርስቲያን ተብሎ አይጠራም፡፡
የይሖዋ ምስክሮች ጥያቄ በጌታ ኢየሱስ ላይ
ጥያቄ ቁጥር 1.ጌታኢየሱስ
በመፅሐፍ ቅዱስ እንደተገለፀው የአብ ልጅ ተብሎ ተጠርቷል ይህ ሲባል አብ ፈጣሪው ነው ማለት ነው
መልስ፡-እነዚህ ሰዎች በመፈጠር እና በመወለድ መካከል ያለውን ልዩነት አልተረዱም
መወለድ ማለት መፈጠር ነው ብለው ነው የተገነዘቡት፡፡በማንኛውም ሁኔታ መፈጠር እና መወለድ አንድ ሁነው አያውቁም ፡፡እስኪ መወለድ
እና መፈጠር ማለት ምን ማለት እንመልከት፡-1.መፈጠር ማለት የሌለን ነገር ካለመኖር ወደመኖር ማምጣት ማለት ነው ለምሳሌ ፡-ሰማይና
ምድር ተፈጠሩ እንጂ ተወለዱ አንልም ካለመኖር ወደመኖር ስለመጡ፤ 2.መወለድ ማለት ካለ ነገር ላይ መገኘት ማለት ነው፡፡
እስኪ አንድ ነገር እንጠይቃቸው እኛን ወላጆቻችን ወልደውናል የእከሌ ልጅ እየተባልን
እንጠራለን ስለዚህ ወላጆቻችን ፈጠሩን ማለት ነው?በፍፁም ነገር ግን ከወላጆቻችን ባህሪ ተካፍለን ተገኝተናል ካለ ነገር መገኘት
ማለት ነው፡፡
ጌታ ኢየሱስ ከአብ ተወለደ ሲባል የአብ ፍጡር ነው ማለት ሳይሆን ከአብ በሀሪ ያለ
ዘመን መቀዳደም ተገኘ ማለታችን ነው፡፡ይህም ሲባል እመቤታችን የ 15 አመት ብላቴና ሳለች ጌታን ወልዳዋለች እናቱ ናት ግን ከሷ
በሀኋላ የመጣ ሳሆን አለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የነበረ ጌታ ነው፡፡
ጥያቄ ቁጥር 2. በመጽሐፈ ምሳሌ
8፡22-31 ባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጥበብ የተባለው ኢየሱስ ‹‹እግዚአብሔር መንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ››ሲል ይደመጣል ይህም
መጀመሪያ የተፈጠርኩት እኔ ነኝ ማለቱ ነው
መልስ 2.አስቀድሞ በ325 ዓ.ም
የተነሳው አርዩስ በኒቂያ ጉባኤ በ318 ሊቃውንት /319 ጌታ ኢየሱስን ጨምሮ/ ሊቃውንት በቅዱስ አትናቴዮስ ክርክር ተረቶ ተወግዞ
የተለየበት ጥቅስ አንዱ ይሔ ነው፡፡እነዚህም ተረፈ አርዮሳውን ይህንንጥቅስ በመጥቀስ ኢየሱስ የአብ የመጀመሪያው ፍጡር ነው ሲሉ
ይደመጣሉ፡፡ እግዚአብሔር መንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ ማለት ፈጠረኝ ማለት አይደለም እስኪ የጥቅሱን ፍሬ ሐሳብ እንየው፡፡
ምሳሌ 8
23ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ።
|
ጥቅሱን በሙሉ ስናነበው ጌታኢየሱስ
አለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ እንደነበረ አለማትም የተፈጠሩት በእርሱ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ
አደረገኝ ሲል እኔን ፈጠረ ማለቱ አይደለም፡፡ጥቅሱን እንፍታው
አብ በወልድ ቃልነት ይህንን
አለም የሚታየውንም የማይታየውንም ካለመኖር ወደመኖር አምጥቶ ፈጠረ ማለት ነው ህንንም ‹‹እግዚአብሔር ብርሀን ይሁን አለ››ዘፍ 1፡3 ሲል ካንደበቱ ቃል ይወጣል
ቃል ኢየሱስ መሆኑ ግልጽ ነው ዮሐ 1፡1-14 በኢየሱስ ቃልነት መፈጠሩን ይገልጽልናል፡፡ማለትም እግዚአብሔር መንገዱን/ፍጥረት መፍጠሩን
/ በኔ ቃልነት በመጠቀም ጀመረ ማለቱ ነው ፡፡
ነገር ግን ኢየሱስ በመጀመሪያ
የተፈጠረ ነው ካልን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንጋጫለን ምክንያቱም በመጀመሪያ ሰማይና ምድር እንደተፈጠሩ አንጂ ኢየሱስ እንደተፈጠረ
አይገልጽም ዘፍ 1፡1
በሚቀጥለው ጊዜ እግዚአብሔር
ቢፈቅድ የሚያነሱትን ጥያቄ አንድ በአንድ እያነሳን መልስ እንሰጥበታለን
ያልገባችሁ ካለ ጥያቄ መጠየቅ
ትችላላችሁ /በሜሴጅም ቢሆን/
የአብ ፀጋ የወልድ ቸርነት የመንፈስ
ቅዱስ አንድነት የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን
ወንድማችሁ ሸዋፈራው አለነ ነኝ
የቃሉን ደጅ ከፍትልኝ ዘንድ
ስለኔ ፀልዩ
ይቆየን
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ