ኢየሱስ ያስታረቀን አማልዶ ወይንስ እዳችንን ከፍሎ?ሊቀካህን ተግባሩስ ምንድነው ማማለድ ወይንስ መስዋእት ማቅረብ?
ይህንን ፅሑፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ነገር በዚህ በፌስ ቡክ ገፅ መናፍቃን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣበትን አላማ ባለመረዳት ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባው እና አማላጅ ነው ብለው ሲፅፉ በመመልከቴ ነው ይባስ ብለውም አጫፋሪዎቻቸው የኛዎቹም ተሀድሶ ነን ባዮችብለው ብለው ይህንን ቃል ደጋግመው ሲናገሩ እንሰማለን እንዲህም ይሉናል ኢየሱስ ያማልዳል ማለታችን አሁን በአብ ዘንድ እየተነሳ እየወደቀ ያማልዳል ማለታችን ሳይሆን አንድ ጊዜ ያፈሰሰው ደሙ እና የቆረሰው ስጋ እየጮኸ ልመናን ያቀርባል ማለታችን ነው ብለው አሻሽለው አዲስ ዶክትሪን ቀርፀዋል፡፡ለመሆኑ ኢየሱስ የሞተው ሊያማልደን ነው ወይስ ሊያስታርቀን ደሙስ አማለደን ነው የምንለው እዳችንን ከፍሎ አስታረቀን መፅሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርገን እንማማራለን ልብ ብላችሁ ፅሑፉን አንብቡ፡፡በመጀመሪያ ማማለድ ማለት በቀላል አማርኛ መለመን ማለት ነው ኢየሱስ አዳም በበደለው በደል የተፈረደበትን ፍርድ ያስወገደው በልመና ፀሎትን በመማቅረብ ሳይሆን እዳውን ከፍሎ በማስታረቅ ነው ማስታረቅ እና መማለድ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ከላይ እንዳልነው ማማለድ መለመን ነው ማስታረቅ ደግሞ አንተም ተው አንተም ተው ብሎ ማቀራረብ ወይም ማገናኘት አልያም አንድን ሰው ወክሎ ያሰው ያጠፋውን ጥፋት በደል መካሻ የሚሆን ካሳ ለተበዳዩ ወገን አቅርቦ ሁለቱን ወገኖች ባቀረበው ካሳ ማገናኘት ወይም ምህረትን ማድረግ ማለት ነው፡፡
መናፍቃኑ እንደሚሉት በአዳም ምክንያት የመጣብን በደል እና ሀጢያት በምልጃ በልመና የሚቀረፍ ወይም የሚወገድ አይደለም በልመና የሚወገድ ቢሆን ኑሮ ብዙ ቅዱሳን አባቶች በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔርን ለምነዋል ወደእርሱም ጩኀዋል ፅድቃችን እንደመርገም ጨርቅ ተቆጠረ በማለት ምሬትን አቅርበዋል ግን ይህ ሁሉ ጩኸታቸው ይህ ሁሉ ልመናቸው ፍፁም እርቅን ድህነትን ሊያመጣላቸው አልቻለም ከመርገም ሊያስወግዳቸው አልቻለም ምክንያቱም ንፁ የሆነ በደል የሌለበት ሰው ተበዳዩን አካል ለብሶ መከራን ተቀብሎ ካሳ መካስ ስለነበረበት ነው ታድያ መርገም በምልጃ በልመና የሚወገድ ቢሆን ኑሮ ቅዱሳኑ በልመና ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ በቻሉ ካህናቱም ህዝቡና ወደእግዚአብሔር ማቅረብ በቻሉ ነበር፡፡ምክንያቱም ያለደም ስርየት ስለሌለ የግድ የደም መስዋእት ያስፈልግ ነበር ካህናቱም ቢሆኑ በእግዚአብሄር ፍቃድ ምንም ሀጢያት የሌለባቸውን ነገር ግን ሰውን ሀጢያት ማስወገድ የማይችሉትን የእንስሳት ደም ያቀርቡ ነበር ግን ይህ መስዋእት ድህነትን ማምጣት አልቻለም ፡፡ፍፁም ድህነት የሚመጣው የበዳዩን የሰው አካል የለበሰ ፍፁም ንፁ የሆነ አካል ደም ሲፈስ ብቻ ነው ፡፡
ከላይ አንደተመለከትነው ኢየሱስ አማልዶ አስታረቀን ማለት ፍፁም ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ኢየሱስ እኛን ያስታረቀን እዳችንን ከፍሎ ፍፁም ራሱን ለሁሉ ቤዛ አድርጎ በመስጠት ነው፡፡ ይህም መፅሐፍ ቅዱሳዊ እውነት እንደሆነ እንመልከት ፡-
1.‹‹ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው››2ቆሮ 5፡18
ከዚ ጥቅስ እንደምንረዳው ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚነግረን ከእግዚአብሔር ጋር ራሱ እግዚአብሄር ከስጋ ጋር ተዋህዶ ከራሱ ጋር እንዳስታረቀን ነው ስለዚህም አማልዶ ለምኖ ሳሆን እርቅ የፈፀመው ዋጋ ከፍሎ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
2.‹‹ ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤›› ሮሜ 5፡10
ይሄ ጥቅስ የተነሳንበትን ሀሳብ ይበልጥ ግልጽ ያደርገዋል ከእግዚአብሔር ጋር ማለትም ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ታረቅነው በኢሱስ ሞት እንደሆነ እርቁም ተፈፀመው በልመና ሳይሆን ራሱን በማቅረብ እንደሆነ ልንገነዘብ ያስፈልጋል፡፡
3. ‹‹ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።›› ኤፌ 2፡16
3. ‹‹እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።›› ቆላ 1፡21;22
ክርስቶስ በሞቱ እንዳስታረቀን ልብ በሉ
4. ‹‹እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።›› ቆላ 1፡19;20
5. ‹‹እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።›› 2ቆሮ 5፡17
መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ክርስቶስ እኛን ከእግዚአብሔር /ከሶስቱ አካላት ጋር/ያስታረቀን አማልዶ ሳይሆን እዳችንን ከፍሎ እንደሆነ ቀጥለን እንመልከት፡፡
1. ‹‹እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤›› ዕብ 1፡3
ልብ በሉ ሀጢያታችንን አማልዶ አነፃ አይልም በስልጣኑ ሀጢያታችንን እንዳነፃ ነው የሚናገረው፡፡
2.‹‹ ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።›› ሮሜ 5፡9
እንግዲህ ደሙ ይለምናል ማለት ምን ያክል ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር እየተቃረኑ እንደሆነ ተመልከቱ በደሙ እንድናለን እንፀድቃለን እንጂ የሚለው ደሙ ይማልድልናል አይልም
3. ‹‹ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ
ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።›› 1ዮሐ 1፡7
እንዴት ያሳርፋል ደሙ ሀጢያትን ያጥባል ተመልከቱ አሁንም ይማልዳል አይልም ደሙ የሰውን ሀጢያት ያጥብ ዘንድ ይቻለዋል፡፡
4.‹‹ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?›› ዕብ 9፡14
የኛ ጌታ ደም ከሀጢያት ሁሉ የሚያነፃ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀን ወደእርሱ ያቀረበን ንጹ ደም ነው ማዳን የሚቻለው ደም ነው ታድያ ደሙ ማዳን ሀጢያታችንን ማጠብ እየቻለ ለምን ለምናል ለምንስ ያማልዳል፡፡
ሊቀካህን ተግባሩ ምንድን ነው?
በብሉይ ኪዳንም ሆነ በእብራውያን መልእክት እንደምናነበው የሊቀካህናት ተግባር የነበረው የእንስሳት መስዋእት ይዞ ቤተመቅደስ በመግባት መጀመሪያ ስለራሱ ሀጢያት በኋላም ስለህዝቡ ሀጢያት እግዚአብሔር ምህረት እንዲያደርግ መስዋእት ያቀርብ ነበር ፡፡ልብ በሉ የብሉይ ኪዳኑ ሊቀካህን መስዋእት በማቅረብ እንጂ ምልጃን በማቅረብ አይደለም ጊዜያዊ የህዝቡን ሀጢያት ያስተሰርይ የነበረው፡፡መስዋእት አቅራቢው ካህኑ መስዋእቱ የእንስሳት ደም መስዋእት ማቅረቢው ታቦቱ እና ለእርሱ ተዘጋጀ ቦታ መስዋእት ተቀባዩ እግዚአብሔር ነበር፡፡ስለዚህም የሊቀካህናት ተግባሩ መስዋእት ይዞ ወደእግዚአብሔር በመቅረብ የህዝቡን ሀጢያት በማስወገድ እንጂ ምልጃ በመያዝ አይደለም፡፡
ኢየሱስም የሀዲስ ኪዳን ዘላለማዊ ሊቀካህናት ሲባል ከብሉይ ኪዳኑ ሊቀካህናት የተሻለ ሊቀካህን ስለራሱ ሀጢያት መስዋእት ማቅረብ የማያስፈልገው ንፁህ ሊቀካህን ዘላለማዊ መስዋእት አንድ ጊዜ ያቀረበ ሊቀካህን ፡፡መስዋእት አቅራቢ ሊቀካህን መስዋእት ተቀባይ ሊቀካህን ራሱን መስዋእት አድርጎ ያቀረበ ሊቀካህን ማለት ነው ያስታረቀንም ዘላለማዊ ሊቀካህንነቱማ ካቀረበው ዘላለማዊ መስዋእት ጋር የተያያዘ እንጂ የሚለምን ምህረት ሚያሰጥ ሊቀካህን ሁኖ አይደለም ፡፡ያም ለዘለአለም ያቀረበውን መስዋእት እስካለም ፍጻሜ እያመኑበት የሚመጡ ሰዎች ሲታረቁበት ይኖራሉ ማለት ነው ፡፡
1.‹‹ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።›› ዕብ 2፡17
የኛ ሊቀካህን ማህሪ ሊቀካህን ነው የኛ ሊቀካህን አቤቱታ አቅራቢ ሳይሆን አቤቱታ ተቀባይ ሊቀካህን ነው መሀሪ ይቅር ባይ ነው፡፡
2. ‹‹ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።›› ዕብ 5፡9
የኛ ሊቀካህን መዳናችንን የሰጠን ሊቀካህን ነው
3.‹‹ ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል››።ዕብ 7፡23-25
የኛ ሊቀካህን አዳኝ ሊቀካህን ነው የኛ ሊቀካህን መሀሪ ሊቀካህን ነው፡፡
አንድ ጊዜ ባፈሰሰው ደሙ ለዘላለም ስንታረቅበት/በስጋውና ደሙ /እንኖራለን ይህ ማለት ምልጃ ማለት አይደለም ያመኑ አዲስ ሰዎች ይታረቁበታል አንድ ጊዜ በአብ ፊት በስጋውና በደሙ በታየው መታየት እንድናለን ማለት ነው፡፡
ወደ ዕብራውያን
7፥27
እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።
9፥12
የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።
9፥26
እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።
9፥27
ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥
9፥28
እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።
10፥10
በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።
10፥14
አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።
ስናጠቃልለው ጌታ ኢየሱስ ያስታረቀን አማልዶ ሳይሆን እዳችንን ከፍሎ ነው ሊቀካህናት መባሉም ዘላለማዊ መስዋእት በማቅረቡ ነው፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለምልጃ የተጠቀሱት ክፍሎች ኢየሱስ ሰው እንደመሆኑ ስጋ እንደለበሰ ለማጠየቅ እና ፀሎትን ለማስተማር ያቀረበው ልመና ነው ፡፡የአብ ሊቀካህናት ጌታችን ሆይ ማረን ይቅር በለን ራራልን፡፡
የአብፀጋ የወልድ ቸርነት የመንፈስቅዱስ ህብረት ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን
ወንድማቹ ሸዋፈራው አለነ

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ