ዓርብ 27 ፌብሩዋሪ 2015



ቢዮንሴና መናፍቃን/ፕሮቴስታንቶች/ ብታምኑም ባታምኑም
በኢየሱስ ስም የሚዋሸው ውሸት ይቁም
          ብታምኑም ባታምኑም ያልኩበት ምክንያት በናፍቃን እውነት ለማመን ስለሚያስቸግራቸው ነው
    ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል እንደሚባለው ብዙ ጊዜ በዚህ በፌስ ቡክ በተደጋጋሚ የምመለከተው መናፍቃን  እውነት እስከሚመስል ድረስ  የሚለቁት የሀሰት ክስ እንቅልፍ ከነሳኝ ሰነባብቷል ፡፡እንደሚታወቀው እነርሱ ከአባታቸው ከዲያብሎስ   የተማሩትን ውሸት በቤተክርስቲያን ላይ ማስተጋባት ከጀመሩ ሰነባብተዋል ፡፡
የዮሐንስ ወንጌል
844
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።

በውሸት ሰብኮ ሰውን ማሳመን የቤተክርስቲያን አላማዋም ተልኮዋም አይደለም ፡፡እውነት የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምህር ሆኖ በዚህ ምድር በሚመላለስበት ጊዜ እውነትን እንጂ ሀሰትን ሲሰብክ አልታየም ቤተክርስቲያንም ከጌታዋ በተማረችው ትምህርት እውነትን ያለሀሰት እየሰበከች እየተናገረች ትገኛለች፡፡ሁላችሁም ይህንን መልእክት የምታነቡ እህትና ወንድሞቼ ትዝ ይላችሁ ከሆነ በኢትዮጵያ  በ2000ዓ.ም/በሚሊኒየም/በአዲስ አመት መንግስት ህዝቡን እንዲያዝናኑ /እንዲያስጨፍሩ/ከጋበዛቸው የውጭ ዘፋኞች መካከል አንዷ ቢዮንሴ ናት፡፡ይህች ሴት በቤተክርስቲያን ተገኝታ ከቀድሞ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ጋር የተነሳችውን ፎቶ በዚህ በፌስ ቡክ በመለጠፍ  ‹‹ለሀጢያተኛዋ ዘፋኝ ታቦት ወጣላት ተዘመረላት ››እያሉ ቤተክርስቲያንን በሀሰት ሲከሱ ሲወነጅሉ አልፎ ተርፎም በአህዛብ/በእስላሞች/ ሲያሰድቡን እንዲሁም በባህር ላይ እንዳለ ኩበት የሚወላውለውን ስጋው/በድኑ/ አካሉ ቤተክርስቲያን መንፈሱ እነእርሱ አዳራሽ የሆነውን ‹‹አማኝ››ሲያጠራጥሩ ለተሀድሶ ክስ መንገድ ሲከፍቱ ተመልክተናል፡፡
     በመጀመሪያ ደረጃ እንድታውቁልኝ የምፈልገው ነገር ታቦት እንኳን ለዘፋኝ ለፓትርያሪክም እንደማይወጣ ታቦት የሚወጣው ለንግስ ጊዜ ብቻ እንደሆነ እና ቤዮንሴ በመጣች ጊዜ ታቦት እንዳልወጣና እንደማይወጣ ነው፡፡እንግዲህ ታድያ ቢዮንሴ ለምን በቤተክርስቲያን ተገኘች ቅዱስነታቸው ከእርሷጋር ለምን ተገኙ ለምንስ አብረው ፎቶ /ቪድዮ/ተነሱ/ተቀረፁ ፎቶ ላየይ እንደሚታየው ለምን ጥላ ወጣ ብላችሁ ለምጠይቁ እውነት ፈላጊዎች እውነቱ ይሄ ነው፡፡ቢዮንሴ ቤተክርስቲያን በተገኘች ጊዜ ቅዱስ ፓትርያሪኩ 17ኛ /በውል ባላስታውሰውም/የሲመት/የተሾሙበት/ፕትርክና/የተቀበሉበትን በአል እያከበሩ ነበር ፡፡እንደሚታወቀው በአለሲመት ሲከበር ጥላ ይወጣል የተሌዩ ሊቃውንት ያሬዳዊ ዜማ ያቀርባሉ ቅኔ ይቀኛሉ እግዚአብሔር ይህንን ስላደረገ ያመሰግናሉ ቢዮንሴም እንዳጋጣሚ በዛ በአል ላይ ስለተገኘች ከመንፈሳዊው በአል ተካፈለች እውነቱ ይሔ ሆኖ ሳለ እንዳባታቸው እንደዲያብሎስ በሀሰት ክስ ቤተክርስቲያንን እየከሰሱ አማኝ ያበዙ መስሎዋቸው በሰተንነታቸው እተጋለጡ ይገኛሉ፡፡
     እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነው እውነቱ ያ ሁኖ ሳለ የዛሬ7 አመት የተካሔደውን ጉዳይ ከ7 ዓመት በኋላ በውሸት ቀምመው ማቅረባቸው የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ሌላው ቢዮንሴ ዘፋኝ ሀጢያተኛ ሁና ሳለ እንዴት ቤተክርስቲያን ተገኝታ በአሉ ላይ ትሳተፋለች ቤተክርስቲያን ውጪ ሀጢያተኛ ነሽ ብላ ልታስወጣት ይገባ ነበር ብሎ የሚጠይቅ ይኖራል፡፡እንደሚታወቀው ቤተክርስቲያን ከጌታ ኢየሱስ በተማረችው ትምህርት መሰረት ሀጢያተኞችን ማግለል ሀጢያተኛ ናችሁ ብላ ከጌታ እንዲርቁ ማድረግ ሳይሆን በፍቅር አቅርባቸው የጌታን ፍቅር እንዲቀምሱ በዚያው ተማርከው እንዲቀሩ ታደርጋለች እንጂ እንደአይሁት ሀጢያተና ዘፋኝ ዘማዊ ናት በድንጋይ ተወግራ ትሙት እያለች መንግስቱን የምትከለክል አይደለችም ጌታ ሁሉን በፍቅር እንደቀረበ ለሀጢያተኛው ሲል እንደሞተ አይሁድ እንኳን ከሀጢያተኛ ጋር ይበላል ብለው ሲከሱት ከሀጢያተኛ እንዳልራቀ ሁሉ መናፍቃን/ዲያብሎሳውያን/ በሀሰት ክስ ቤተክርስቲያንን ቢከሱም ሀጢያተኖችን ሂዱ ከዚህ ብላ በዲያብሎስ ምክር የምታባርበት ምክንያት የለም በፍቅር ቀርባ ወደእግዚአብሔር ፍቅር እንዲገቡ በፍቅር ታስገድዳቸዋለች፡፡
የማቴዎስ ወንጌል
911
ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን። መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው።


የሉቃስ ወንጌል
152
ፈሪሳውያንና ጻፎችም። ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ።


     እንግዲህ ጌታኢየሱስን ለምን ቀራጩ ዘኪዮስ ቤት ገባህ ለምን ዘማዊቷ ሴት በድንጋይ እንዳትወገር ከለከልክ ለምን ከሀጢያተኞች ጋር ትበላለህ ትጠጣለህ ሀጢያተኖችንስ በፍቅር ለምን ትቀርባለህ ለሀጢያተኞች ለምን ሞትክ ብለው እንደማይጠይቁ ሁሉ በክርስቶስ ደም የተዋጀችውንም ቤተክርስቲያን ጌታዋን አብነት አድርጋ በምትሰራው ስራ ሊጠይቋት አይገባም ባይ ነኝ ፡፡የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን ፡፡
የዮሐንስ ወንጌል
810
ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ። አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት።

የዮሐንስ ራእይ
1210
ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።አሜን


የአብ ፀጋ የወልድ ቸርነት የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
ሻሎም/ሰላም/
                      ወንድማችሁ ሸዋፈራው አለነ ነኝ
በፀሎታችሁ አስቡኝ


ይድረስ ለፕሮቴስታንቶች
መጽሐፍ ቅዱስ እና መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የሚለው አስተምህሮ
SOLA SCRIPTURA
ከተሐድሶ /Reformation/ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ፕሮቴስታንቶች መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ (Sola Scriptura) የሚል መመሪያ መከተል ጀመሩ፡፡ ነገር ግን ይህ መመሪያ ራሱ በየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ አይገኝም፡፡
ይህ ነገር ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ከተፈለገ (ማለትም ከቤተ-ክርስቲያን ሕያው የትውፊት ምስክርነት፣ ከቤተ-ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን የመተርጎም ሥልጣን እና ስጦታ በተለየ ወይም እነዚህን ሳንመለከት ለመዳን አስፈላጊ ሆነው ለእግዚአብሔር የተገለጡት ነገሮች ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ተጠቃለው ይገኛሉ ካልን) Sola Scriptura ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የሚለው አስተምሕሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጦ መገኘት ነበረበት፤ ነገር ግን ይህ በየትኛውም ክፍል አይገኝም፡፡
ከዚህ አስተምሕሮ በተቃራኒ መጽሐፍ ቅዱስ በየትኛውም ቦታ ለክርስቲያኖች ዋነኛ፣ በቂ እና ሌላ ተጨማሪ ድጋፍ የማያስፈልገው (በርካታ ፕሮቴስታንቶች እንደሚያስቡት) የእምነት መመሪያ ስለመሆኑ አያብራራም፡፡ ይልቁም መጽሐፍ ቅዱስ የራሱን አስፈላጊነት እና ሥልጣን እንዲሁም የተቀደሰውን ትውፊት እና የቤተ-ክርስቲያንን አስፈላጊነት እና ሥልጣን ይገልጻል፡፡ ማቴ.16፡18-19 ‹‹እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚህችም ዐለት ላይ ቤተ-ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆች አይችሏትም፡፡ የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፡፡ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል፡፡›› 
ማቴ.18፡17-18 ‹‹ደግሞም ቤተ-ክርስቲያንን ባይሰማት እንደ አረመኔ እና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ፡፡ እውነት እላችኋለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፡፡ በምድርም የምትፈቱት በሰማያት የተፈታ ይሆናል››
ሉቃ.10፡16 ‹‹የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል፡፡››
መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ Sola Scriptura (መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ) የሚለውን መመሪያ እንደማያስተምር ነቅሰው በማውጣት ከሚያሳዩን የአዲስ ኪዳን ክፍሎች በተጨማሪ ‹‹የካህናትን›› የማስተማር ሥልጣን አንቀበልም የሚሉ እና ከእግዚአብሔር ሥልጣን ለተሰጣቸው ለእነዚሁ ካህናት የማይታዘዙትን በሚመለከት በብሉይ ኪዳን የማስጠንቀቂያ ቃል እናገኛለን፡፡ በዚህ የብሉይ ኪዳን ክፍል እንደምናገኘው እግዚአብሔር ካህናቱ ሕጉን (ሃይማኖታዊ ሕግ፣ ማህበራዊ ሕግ፣ የወንጀል ሕግ) ይተረጉሙ ዘንድ የሚያስችላቸውን ሥልጣን ሰጥቷቸዋል (ዘሌ.20፡1-27፣         )፡፡
ይህም ሥልጣን በሕጉ ትርጓሜ ላይ ተመሥርተው የመወሰን እና የመፍረድ ሥልጣን ጭምር ነው፡፡ ዘዳ.17፡8-13 ‹‹በደም እና በደም በፍርድ እና በፍርድ በመቁሰል መካከል በአገርህ ደጅ ውስጥ ስለሚከራከሩት ክርክር የሚሣንህ የፍርድ ነገር ቢነሣ አንተ ተነሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደመረጠው ሥፍራ ትወጣለህ፤ ወደ ሌዋውያን ካህናት በዚያም ዘመን ወደ ተሾመው ፈራጅ መጥተህ ትጠይቃለህ፤ እነርሱም የፍርዱን ነገር ይነግሩሃል፡፡ እግዚአብሔርም ለመረጠው ሥፍራ የነገሩህን የፍርድ ነገር ታደርጋለህ፤ እንዳስተማሩህም ታደርግ ዘንድ ጠብቅ፡፡ እንዳስተማሩህም ሕግ እንደነገሩህም ፍርድ አድርግ፤ ከነገሩህም ፍርድ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፡፡ ማናቸውም ሰው ቢኮራ፤ በዚያም አምላክህን እግዚአብሔርን ለማገልገል የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ለመስማት ባይወድድ ይሙት፡፡››
ከዚህ ጋር በተመሳሳይ ከላይ ያየናቸው ክፍሎች ለይተው እንዳስቀመጡት እግዚአብሔር የካህናትን ሥልጣን በማስተማር (ማቴ.28፡20)፣ መጽሐፍ ቅዱስን በመተርጎም (የሐ.ሥ.2፡14-36) በማሰር እና በመፍታት (ማቴ.18፡18፣ የሐ.ሥ.15፡28-29) እናም ደግሞ በእርሱ ስም በተሰጣቸው የማስተማር ሥልጣን ቀብቷቸዋል (ሉቃ.10፡16)፡፡
ይሁዳ 10-11 ‹‹እነዚህ ሰዎች ግን ለማስተዋል ያቃታቸውን ነገር ሁሉ ይሳደባሉ፤ አዕምሮ እንደሌላቸው እንስሶች በተፈጥሮ ስሜት የሚያውቁት ነገር ቢኖር እንኳ በእርሱ ይጠፋሉ፡፡›› ካለ በኋላ በጣም ጠንከር ባለ ድምፅ እንዲህ ያስጠነቅቃል ‹‹በቃየል መንገድ ስለሄዱ፣ ለገንዘብ ብለው በበለዓም ስህተት ስለወደቁ፣ ቆሬም እንደተቃወመ ስለተቃወሙ በመቃወማቸው ስለጠፉ ወዮላቸው!›› (11.12)
‹‹የቆሬ ዐመጽ›› (ቆሬ የአብርሐም የልጁ ልጅ ነበር) ብሎ ይሁዳ የሚናገረው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኦሪት ዘኁልቅ 16፡1-35 የተገለጸው ነው፡፡ ቆሬ እና ወገኖቹ ሕጋዊና ተገቢ በሆነው በሙሴ እና በካህናቶቹ ሥልጣን ላይ አምጾ ነበር፡፡
ሌሎች የተጠቀሱ ቦታዎች፡- 1ኛቆሮ.10፡8፣ 1ኛቆሮ.11፡2፣ 1ኛተሰ.2፡13፣ 1ኛተሰ.2፡15፣ 1ኛ ጢሞ.3፡14-15፣ 2ኛጴጥ.3፡15-17፣ 2ኛጴጥ.1፡20-21፣ 2ኛጴጥ.2፡1
‹‹የእግዚአብሔር ቃል›› ማለት ሁልጊዜ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ›› ብቻ ማለት አይደለም
አንዳንድ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹የእግዚአብሔር ቃል›› የሚለውን አገባብ መጽሐፍ ቅዱስን ለማለት የገባ አድርገው ያስቡታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ግን እንደዚያ ለማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ኢየሱስን፣ በቃል የሚተላለፈውን ስብከተ ወንጌል፣ የመልእክትን ቃል ጭምር ያሰማል።
ኢሳ.55፡10-19 ‹‹ዝናብ እና ደቂቅ በረዶ ከሰማይ ወርደው ምድርን በማርካት ፍሬ እንደምታፈራ እንደሚያደርጋትና ለዘሪው ዘርን፣ ለበላተኛውም ምግብን ሳይሰጡ ወደ ሰማይ እንደማይመለሱ ከእኔ አንደበት የሚወጣውም ቃል እንደዚሁ ነው፡፡ እርሱ የላክሁትን ጉዳይ ሳያከናውንና ተልዕኮውን ሳይፈጽም ወደ እኔ አይመለስም፡፡››
ሉቃ.3፡2-3 ‹‹በዚህ ጊዜ የዘካሪያስ ልጅ ዮሐንስ በበረሐ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ፡፡ ስለዚህ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ባሉት አገሮች ዙሪያ ‹ለኃጢአታችሁ ይቀርታ እንድታገኙ ንስሐ ገብታችሁ ተጠመቁ› እያለ ያስተምር ነበር፡፡››
ሌሎች የተጠቀሱ ቦታዎች፡- ሉቃ.4፡44፡5፡1፣ 1ተሰ.2፡13፣ ሉቃ.8፡11-15፣ ዕብ.4፡12-13፣ ዮሐ.1፡1፣14፣ ዕብ.11፡3፣ የሐ.ሥ.4፡31




ምክር ለሙስሊሞች  /ለመሀመዳውያን/
  በዚህ በፌስ ቡክ ብዙ ጊዜ በመፅሐፍ ቅዱስ እና በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን  በኢየሱስ ክርስቶስ ዙሪያ የኢየሱስ አማኞች የሆነውን በክርስቶስ ስሙ ክርስቲያን የተባልነውን ጥያቄ ትጠይቃላችሁ ፡፡ ለጥያቄያችሁም በቂ መልስ ስንሰጣችሁ የመፅሐፍ ቅዱስ እና የኢየሱስ አማኞች እኛ ሁነን ሳለ ራሳችሁን መፅሐፍ ቅዱስን እንደተረዳ እና ስለኢየሱስ ማንነት አዋቂ አድርጋችሁ በመቁጠራችሁ ምክንያት የሰጠናችሁን መልስ ባለመቀበል የመፅሐፍ ቅዱሱን ትርጓሜ ይህ አይደለም አንቀበላችሁም ይህ ክፍል ለመናገር/መልእክት ለማስተላለፍ/የፈለገው እንዲህ የሚል ነው እያላችሁ በኮሜንት አስተያየታችሁን ስትሰጡ አያለሁ፡፡በመሰረቱ መፅሐፍቅዱስን የምናምነው እኛ እንጂ እናንተ አይደላችሁም ስለመፅሐፍ ቅዱስም ትርጉም የምናውቀው እና እንጂ እናንተ አይደላችሁም ፤ስለኢየሱስ ማንነት መናገር ያለበትም አማኙ እንጂ ፍፁም ክህደት ያለባችሁ እናንተ አይደላችሁም ፡፡ስለዚህም የፈለጋችሁትን በኢየሱስ ላይም ሆነ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ ብሎም በእምነታችን ላይ ጥያቄ መጠየቅ ትችላላችሁ የምንሰጣችሁን መልስ በጥሞና አዳምጣቹ/አንብባቹ/ ወደእውነቱ ከመምጣት ይልቅ ትችት ውስጥ መግባት አስፈላጊ አይደለም ባይ ነኝ ፡፡
የክርስቶስ ሰላም ከናንተጋር ይሁን
ወንድማችሁ ሸዋፈራው አለነ
ክርስትና ማስቀደስ ሳይሆን መቀደስ ነው ለሚለው ኑፋቄ የተሰጠ ምላሽ?
ብዙ ጊዜ ፕሮቴስታንት ወገኖቻችን ይህንን ቃል ደጋግመው ሲያነሱ እና እውነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስመስለው ፌስ ቡክ ላይ ሲለቁት ተመልክታችሁ ይሆናል፡፡ይህንንም የሚያደርጉበት ምክንያት ቤተክርስቲያንን ለመቃወም እና ምእመኑን ከእውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን ለማውጣት እና ለዲያብሎስ ለማስረከብ በማሰብ ነው፡፡ቤተክርስቲያናችን ዘወትር እግዚአብሔርን በልቧ በተግባርና በአምልኮ ስርአቷ ትቀድሰዋለች /ታመሰግነዋለች/፡፡ቅዳሴ ማለት ምስጋና ማለት ነው ፡፡መናፍቃን ግን ለመተቸት ‹‹ክርስትና ማስቀደስ ሳይሆን መቀደስ ነው››እያሉ ሲፎክሩና ሲሸልሉ በሀይማኖት ያልበሰሉትንም ሲያደናግሩ እንመለከታለን መጽሐፍ ቅዱስ ስለቅዳሴ/ጌታን ስለመቀደስ ምን ይላል እስቲ እንመልከተው፡፡
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት
3፥15
ሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።
ትንቢተ ኢሳይያስ
8፥13
ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን።
የማቴዎስ ወንጌል
6፥10
ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
ኦሪት ዘኍልቍ
20፥12
እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም አላቸው።
የሉቃስ ወንጌል
11፥2
አላቸውም። ስትጸልዩ እንዲህ በሉ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
ታዲያ ቤተክርስቲያን ምን አጠፋች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባገኘችው ቃል ነው ቅዳሴ የምትቀድሰው/ጌታን የምታመሰግነው/
ለምትሰጡኝ አስተያየት መጽሀፍ ቅዱስ እንጂ ትችት እንዳይሆን
ጌታ ለመናፍቃኑ ልቦና ይስጣቸው

ሐሙስ 26 ፌብሩዋሪ 2015

እመቤታችን ሆይ የሚለው ፀሎት ከየት መጣ
አንድ እህቴ እንዲህ በማለት ጥያቄ
ጠየቀቺኝ እናተ ኦርቶዶክሶች ስትፀልዩ
አባታችን ሆይ ካላቹ በሀላ እመቤታችን
ብላቹ እምትፀልዩት ፀሎት
ፍፁም ከመፅኀፍ ቅዱስ ውጪ ነው
ስለዚህ መፀለይ የለበትም አለቺኝ

.
.
እንግዲህ እኛም ተዋህዶ እንዳስተማረችን
የተወደደች እናታችንን
እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን
እንጠራታለን
እንዲህም እንላለን፦
.
እመቤታችን ንፅህት
ቅድስት ድንግል (ማቴ1:23)
ማሪያም ሆይ(2ቆሮ11:2)
በመልአኩ በቅድስ ገብርኤል ሰላምታ
ሰላም እንልሻለን (ሉቃ1:28)
በሀሳብሽ ድንግል ነሽ (2ቆሮ11:2
ንፅህት )
በሥጋሽም ድንግል ነሽ(ማቴ1:23)
(ህዝ44:2)
ያሸናፊ የልዑል እናት ሆይ (ሉቃ1:35)
ሰላምታ ላንች ይገባሻል
ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንች የተባረክሽ ነሽ
(ሉቃ1:28 ናሉቃ1:32)
የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው (ሉቃ1:32)
ፀጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ
ልዑል እግዚአብሔር ካንች ጋር ነውና
(ሉቃ1:28-30)
ከተወደደው ከልጅሽ ከጌታችን
ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ
ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን
በቆሮ5:20
በፅድቅ ስራ የኖሩት ይለምኑ ዘንድ
ተሰጥቷቸዋልና
ሃጢአታችንምያስተሰርይ ዘንድ ለዘላለሙ
አሜን።
.
.
እኛም ይህን ከመፀለይ ቸል ብለን
የእናታችንን ውለታ አንረሳም፡፡
ነገር ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተዋህዶን
ሊተቹ የሚነሱትን እግዚአብሔር ልቦና
ይስጣቸው፡፡ አሜን፡
ጸሎተ ፍትሐት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ዓለም በደሉ ይቅር አይባልለትም ማለቱ በዚህ ዓለምና ለሚመጣው ዓለም ይቅር ሊባል የሚችልና ይቅር ሊባል የማይችል ሁለት የኃጢአት ዓይነት መኖሩን ይመላክተናል፡፡ (ማቴ፡-12÷32) በዚህ አባባል መሠረት በሚመጣው ዓለም ኃጢአት ይቅር የሚባል ከሆነ ጸሎተ ፍትሐት ጠቃሚ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶ ለነበረው ለኦኔሲፎር ‹‹በመጨረሻው ቀን ጌታ ምሕረትን ይሰጠው ›› ብሎ ጸልዮለታል (2ጢሞ፡-1÷18) ኦኔሲፎረም በሕይወት ያልነበረ መሆኑ የሚታወቀው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሌሎች ሰላምታ ሲይቀርም ለእርሱ ግን የጸለየለት በመሆኑ ነው ለሞቱ ሰዎች መጸለይ የማያስፈልግና ጥቅም የሌለው ቢሆን ኖሮ ታላቁ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለሞተ ሰው ባልጸለየ ነበር፡፡
(ለሞቱ ሰዎች መጸለይ (ጸሎተ ፍትሐት) በብሉይ ዘመንም የነበረ እንጂ በሐዲስ ኪዳን የተጀመረ አይደለም፡፡ ጀግናው መቃብዮስ በጦርነት ለሞቱ ወታደሮቹ የኃጢአት መስዋዕት ይደረግላቸው ዘንድ ሁለት ሺህ የብር ድራህማ አሰባስቦ ወደ ኢየሩሳሌም የላከ መሆኑን በ2ኛው መጽ.መቃ. 12÷43 ላይ ይጠቅሳል፡፡ የሐዋርያት ትምህርት የሆነው ዲድስቅልያ ‹‹...በጌታ ተስባስባችሁ ዘምሩላቸው በየአብያተ ክርስቲያናችሁ የቅዳሴ ጸሎት አድርጉ...›› (ዲድ አንቀጽ 33) በማለት ይገልጸዋል፡፡ የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው እንዲል ዘማሪው ዳዊት (መዝ 116÷115) በየአብያተ ክርስቲያናት በየዕለቱ በሚደረገው የቅዳሴ ጸሎት መካከል ለሙታን የሚጸለይ በመሆኑ ይህም ለሙታን የመጸለይ ሥርዓት ከጥንት ጀምሮ ሲሠራበት የኖረ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡
(.ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች በተላከው የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ላይ ባደረገው 41ኛው ስብከቱ፡- ‹‹...አንድ ሰው ኃጢአተኛ እንደሆነ ቢሞት የምንችለውን ያህል ልንረዳው ይገባል፡፡ የምንረዳውም በልቅሶና በኃዘን ሳይሆን በጸሎት በምጽዋትና በቁርባን ነው፡፡ የዓለምን ኃጢአት ወደተሸከመው የእግዚአብሔር በግ ስለሙታን የምንጸልየው እነርሱ መጽናናትን ዕረፍትን እንዲያገኙ ብለን ነው እንጂ በከንቱ አይደለም፡፡ ጻድቁ ኢዮብ ስለልጆቹ ያቀርብ የነበረው ቁርባን ጠቀሜታ ከነበረው ስለሙታን የምናቀርበው ቁርባን ምንኛ የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረው?›› በማለት ገልጾታል፡፡ (የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትምህርተ መለኮት 3ኛ መጽሐፍ ገጽ 508-509 በሚካኤል ሚና)
(.ነፍስ ከሥጋ እንደተለየች የመጨረሻ ዋጋዋን የምትቀበለው ወዲያው ሳይሆን በዕለተ ምጽአት በመሆኑ ለሰው ልጅ ሁሉ ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር አምላክ ያወርሳቸው ዘንድ በሕይወት ለሌሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በእምነት በመሆን የፍትሐት ጸሎትን እናደርግላቸዋለን ፡፡
ታላቅ ጠቀሜታ አለውና (ፍትሐ ነገሥት አንቅጽ 22 ) በዚህ መሠረት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ለሙታን የጸሎት ፍትሐት ሥርዓት በአግባቡ ትፈጽማለች፡፡
ሦስቱ የቅድስና መንገዶች በመባል የሚታወቁት ጥምቀት፣ ሥራና ሹመት ናቸው፡፡ እንደአለቃ አያሌው ታምሩ አገላለጽ የሰው ልጅ የቅድስና መንገዶች ከሦስቱ ውጭ እንደማይሆኑ ይጠቁሙናል፡፡ ቀጥሎም በተናጠል ለመመልከት እንሞክራለን፤
ሀ/ ቅድስና በጥምቀት፡- በጥምቀት ልጅነት ማግኘት የእግዚአብሔር ልጅ በሥጋ የሰው ልጅ ስለሆነ በእርሱ ሰጭነት በእርሱ ቤዛነት የሰው ልጅ ደግሞ በጸጋ በእግዚአብሔር ልጅ ይሆን ዘንድ ደግሞ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለድ ነውና የእግዚአብሔር ልጅ በሥጋ የሰው ልጅ ስለሆነ በእርሱ ሰጭነት በእርሱ ቤዛነት የሰው ልጅ ደግሞ በጸጋ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆን ዘንድ ደግሞ ከውኃና ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ይወለድ ዘንድ አስፈልጐታል በጥምቀት፡፡ (1ኛ ቆሮ፡- 1÷2፣ ኤፌ፡- 1÷1)
ለ/ ቅድስና በሥራ፡- ሰውነትን ለእግዚአብሔር በመለየት ፣ በስሙ ለተቀበሉት እምነት መስዋዕት አድርጐ በመስጠት የሚገኝ ቅድስና ነው፡፡ ለእግዚአብሔር የተሰጡ ፣ ለእግዚአብሔር የሆኑ፣ ለእግዚአብሔር የተለዩ ሁሉ በብሉይ ኪዳን ናዝራዊያን ይባሉ ነበር፤ ለምሳሌ፡- መስፍኑ ሶሞሶን ይጠቀሳል፡፡ (መጽ.ምሣሌ፡- 13÷5) በዚህ ስም በሐዲስ ኪዳንም ጌታችንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተጠርቶበታል፡፡ (ማቴ፡- 2÷23) ይህንን መሠረት በማድረግ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹...የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም በሥራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ›› (1ኛ ጴጥ. 1÷15) በማለት መልእክቱን ጽፏል፡፡
ሐ/ የቅድስና ጸጋ በሹመት፡- በክርስትና የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን የታደሉ ክርስቲያኖች በእምነታቸው በምግባራቸው ከሚያገኙት ጸጋ ሌላ አሁንም በእምነታቸው፣ በምግባራቸው መልካምነት ተመርጠው በሹመት የሚገኙት ቅድስና አለ፡፡ አብ የመረጠውና የቀደሰው ወልድ ለሰው ያሰበውን የፈቀደውን ቤዛነት ሥራ በሞት ካተመ በትንሣኤው ከደመደመ በኋላ በሹመት የሚያገኘውን ከፍተኛውን ሥልጣንና ቅድስና ለመረጣቸው ለጠራቸው እርሱን እንዲመስሉ ለአዘጋጃቸው ለሰው ልጆች ሰጥቷል፡፡ ይህም ሥልጣን ማጥመቅ፣ ለማሰር፣ ለመፍታት፣ ተአምራትን ለማድረግ፣ ለመሾም፣ ለመሻር፣ ኃጢአትን ለማስተሰረይ፣ ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት /ለማውጣት/ መስዋዕት ለማቅረብ የቅድስና ሹመት ሰጥቷቸዋል፡፡ (ዮሐ፡- 17÷17-20፡ ማቴ፡- 28÷18-20፣ ማር፡- 16÷15-20፣ ሉቃ፡- 24÷49-53)
ትምሕርተ ሃይማኖት/ክፍል 5/
ምሥጢረ ሥጋዌ
ሥጋዌ : ተሰገወ ሰው ሆነ ካለው የተገኘ ሲሆን : ምሥጢረ ሥጋዌ ማለት ሰው የመሆን ምሥጢር ማለት ነው ።
በዚህ ትምህርታችን አምላክ
- ለምን ሰው ሆነ ?
- እንዴት ሰው ሆነ ?
- ከማን ተወለደ ?
- የት ተወለደ ? የሚሉትን በዝርዝር እንማራለን ።
አምላክ ለምን ሰው ሆነ?
1 አዳምን ከበደል ሊያነጻው
አዳም የሰይጣንን ምክር በመስማት እግዚብአሔር አትብላ ያለውን ዕፀ በለስ በልቶ ትእዛዙን በማፍረሱ ከፈጣሪው በተጣላ ጊዜ የሞት ፍርድ (ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ) ተፈረደበት ። ዘፍ 3 ፥ 1 ። ለጥፋቱ ምክንያት የነበሩት ዕባብና ሄዋንም እንደ ጥፋታቸው መጠን ተረግመዋል ። ዘፍ 3 ፥ 14 ።
አዳምም ጥፋቱን አምኖ ንስሓ ስለገባ አምላክ ሰው ሆኖ እንደሚያድነው ቃል ገባለት ። ዘፍ 3 ፥ 22 ። ቃል ኪዳኑም “አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” የሚለው ሲሆን እግዚአብሔር ወልድ በተለየ ስሙ ፣ በተለየ ግብሩ ፣ በተለየ አካሉ ፣ ሰው ሆኖ እንደሚ ያድነው ቃል መግባቱን ይገልጻል ።
ለአዳም በገባው ቃሉ መሰረት ጊዜው ሲደርስ ከተፈረደበት ፍርድ ነፃ ሊያወጣው (ሊያድነው) ሰው ሆነ ። ገላ 4 ፥ 4 ። ጊዜው ማለት አምስት ሺህ አምስት መቶ (አምስት ቀን ተኩል ሲፈጸም) ማለት ነው ። መዝ 84 ፥ 4 ።
2 የሥጋን በደል ለመካስ
- አዳም ፤ ዕፀ በለስን በበላህበት ቀን ሞትን ትሞታለህ ዘፍ 2 ፥ 17 ። ያለውን አምላካዊ ቃል ተላልፎ በለስን በመብላቱ የሞት ፍርድ ከተፈረደበት በኋላ ንስሃ በመግባቱ ፤ አምላክ ትሞታለህ ያለው ፍርዱ ሳይሻር ይቅር ይለው ዘንድ ወደደ ። በመሆ ኑም በመለኮታዊ ባህርዩ ሞት ስለማይስማማው የሚሞት ሥጋን ለብሶ(ሰው ሆኖ) ቅጣቱን ሊቀበልለት ። ኢሳ 53 ፥ 1 ።
- የእግዚአብሔር ቸርነቱ የባህርዩ ስለሆነ ፤ ሞቱን ሞቶ ፍርዱን በመፈጸም ፤ ይቅር ብሎ ቸርነቱን በማድረግ ፤ ፍርዱንም ፤ይቅር ባይነቱንም ፤ በአንድ ጊዜ ሊገልጽ ፈቃዱ ስለሆነ ።
3 ፍቅሩን ለመግለጽ
እኛ ሰዎች ምንም ያህል ሰውን ብንወድ ቁሳዊ ነገር ልንሰጥ እንችላን ። እርሱንም ቢሆን ጥቅማችንን (ትርፋችንን)አይተን ነው ። አምላካችን ግን ከእኛ ምንም ላያገኝ ባህርዩን ዝቅ አድርጎ ደካማ ባህርያችችንን በመዋሃድ በአዳም የተፈረደውን ፍርድ እርሱ ተቀብሎ በማዳን እውነተኛ ፍቅሩን ሊገልጽልን ስለወደደ ። ዮሐ 15 ፥ 13 ። ዮሐ 10 ፥ ፲፩ ። ኢሳ 40 ፥ 11 ።
እንዴት ሰው ሆነ ?
1. የሚወለድበት ጊዜው ከመድረሱ አስቀድሞ በነቢያት አድሮ እንዴት እንደሚወለድ ምሳሌ አመስሏል ትቢት አናግሯል ።
ምሳሌ
- የመልከ ጼዴቅ ክህነት ።መልከ ጼዴቅየጌታ ፤ አብርሐም የምዕመናን ። ዘፍ 14 ፥ 18 ። ዕብ 7 ፥ 1 ።
- የይስሐቅ ቤዛ ሆኖ የተሰዋው በግ ። ዘፍ 22 ፥ 18 ። ይስሐቅ የአዳም ፣ በግ የጌታ ምሳሌ ። ዮሐ 1 ፥ 29 ።
- የእሥራኤል መና ። ዘፀ 16 ፥ 13 ። እሥራኤል የአዳም ፣ መና የጌታ ምሳሌ ።
ዮሐ 6፥ 32 ። ግብፅ የሲኦል ፤ ከነዓን የመንግስተ ሰማያት ፤ ባህረ ኤርትራ የኃጢአት ፤ የሙሴ በትር የመስቀል ፤ ምሳሌ ሲሆን ፤ ሌሎችም በርካታ ምሳሌዎች አሉ ።
ትንቢት
- እግዚአብሔር በሴም ቤት ይደር ። ዘፍ 9 ፥ 26 ። እግዚአብሔር የተባለው ወልድ ፤ ቤት (ድንኳን) እመቤታችን ።
- በዘርህ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ። ዘፍ 20 ፥ 17 ። ዘር የተባለ ጌታ ፤ አሕዛብ የተባሉ የሰው ልጆች ። ገላ 3 ፥ 16
- ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል ። ዘኁ ፳፬ ፥17 ። ኮከብ የጌታ ፤ ያዕቆብ የሰው ልጅ (የሰው ባህርይ) ። ማቴ 2 ፥ 7 ።
2. ብስራተ መልአክን በተቀበለችበት ሰዓት
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ባበሰራት ጊዜ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ ብላ ስትቀበል ቃሏን ምክንያት አድርጎ መለኮታዊ ባህርዩን ከሰው ደካማ ባህርይ ጋር በማዋሀድና ከሁለት አካል አንድ አካል ፤ ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ በመሆን ፍፁም ሰው ፤ ፍፁም አምላክ ሆነ ። ይህም ማለት መለኮታዊ ባህርዩን ከሰው ባህርይ ጋር አንድ አድርጎ(አዋህዶ) ሰውና አምላክ (ፍጹም ሰው ፤ ፍጹም አምላክ) ሆነ ። ሉቃ 1 ፥ 30 ። ማቴ 1 ፥ 23 ። ዮሐ 1 ፥ 14 ።
3. ሲዋሃድም
- እንበለ ውላጤ ፤ ያለ መለወጥ ። እንደ ሎጥ ሚስት ። ዘፍ 19 ፥ 26 ። እንደ ቃና ውሃ ። ዮሐ 2 ፥ 1 ። ያይደለ ።
- እንበለ ቱሳሄ ፤ ያለመቀላቀል ። እንደ ማርና ውሃ ሳይቀላቀሉ ፤ በመጠባበቅ ቃልም ሥጋም ባህርያቸው ሳይለወጥ ።
- እንበለ ቡዓዴ ፤ ያለ መለያየት ። እንደ ጥሬ እህል መለያየት ሳይኖር ከሥጋዌ በኋላ በተዋህዶ ይኖራል ።
- እንበለ ኅድረት ፤ ያለ ማደር ። እንደ ልብስና ሳጥን ሳይሆን ፤ እንደ እሳትና እንደ ብረት ባለ ተዋሕዶ ።
- እንበለ ትድምርት ፤ ያለ መጨመር ። ዕቃ በዕቃ ላይ እንደሚደራረብና ሲፈለግ እንደሚለያይ ሳይሆን ፤ መለኮቱ ከትስብዕቱ (ከተዋሃደው ነፍስና ሥጋ) ጋር በፍፁም ተዋሕዶ አንድ በመሆን ተወለደ ።
ከማን ተወለደ?
አምላክ የተወለደው ከእመቤታችን ሲሆን ፤ ከሷ እንደሚወለድም ፤ በእግዚአብሔር መነንፈስ በተቃኙ ቅዱሳን አማካኝነት አስቀድሞ ፤ ምሳሌ ተመስሏል ፤ ትንቢት ተነግሯል ።
ምሳሌ
- እግዚአብሔር በሴም ድንኳን ይደር ። ዘፍ 9 ፥ 26 ። ድንኳን የእመቤታችን ፤ እግዚአብሔር ሰው የሆነው ጌታ ምሳሌ ።
- የአብርሐም ድንኳን ። ዘፍ 10 ፥ ፲፰ ። ድንኳን የእመቤታችን ፤ በአብርሐም ቤት የተስተናገደው እንግዳ የራሱ ጌታ ምሳሌ
- የያዕቆብ መሰላል ። ዘፍ 28 ፥12 ። መሰላል የእመቤታችን ፤ በመሰላሉ ላይ የተቀመጠው ንጉሥ የክርስቶስ ምሳሌ ።
- የሙሴ ዕፅ ፥ሐመልማልና ነበልባል ። ዘፀ 3 ፥ 2 ። ሐመልማል የእመቤታችን ነበልባል የመለኮት ምሳሌ ። ውዳ ማር ።
- የሙሴ ጽላት ። ዘፀ 31 ፥ 18 ። የጽላቱ ማደሪያ የሆነው ታቦት የእመቤታችን ፤ ጽላት የጌታ ምሳሌ ።
- የጌዴዎን ፀምርና ጠል ። መሳፍ ፮ ፥ 36 ። ፀምር የእመቤታችን ፤ ጠል የጌታ ፤ ምሳሌ ።
ትንቢት
“ሄዋን ትባል ” ። ዘፍ 2 ፥ 22 ። ሄዋን ማለት እመህያዋን ማለት ነው ። ይህ ስም የተሰጠው ለእመቤታችን ነው ። የመጀ መሪያዋ ሄዋን ሞትን ያመጣች ስትሆን ፤ እመቤታችን ግን የሕይወት ባለቤት የሆነው ጌታ ከእሷ ስለተገኘ መሠረተ ሕይወት የሕይወት መገኛ ብለን እንጠራታለን ። መዝ 45 ፥4 ። ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ ። ልዑል የተባለው አምላክ ሲሆን ፤ ማደሪያው የተባለች ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህፀኗ ተሸክማ የወለደችው የአምላክ እናት እመቤታችን ናት ።
- የተቆለፈች ገነት ። መኃ 4 ፥ 45 ። ይህ እመቤታችን አምላክን በድንግልና መውለዷንና ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን የሚያስረዳ ሲሆን ፤ በተጨማሪም በህዝቅኤ 44 ፥ 1 ። ላይ ያለው ይህን ግልጽ ያደርገዋል ።
- እነሆ ድንግል ወልድን ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል። ኢሳ 7 ፥ 14 ። ይህ ቃል በቀጥታ የእመቤታችንን የአምላክ እናትነቷን ይገልጻል ። ድንግል የተባለች እሷ ፤ ወልድ (ልጅ) የተባለ ልጇ አማኑኤል ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ።
የነቢያት ትንቢት ሲፈጸም ፤ በህጋዊና በተቀደሰ ጋብቻ ከሚኖሩ ኢያቄምና ሐና በብሥራተ መልአክ እመቤታችን እንድት ወለድ አደረገ የተወለደችውም አዳምና ሄዋን ሳይበድሉ በነበራቸውና መርገም (ጥንተ አብሶ የመጀመሪያ በደል) ባልተላለፈበት ንፁህ አካል ነው ። ከእሷ የሚወለደው አምላክ ለባህርዩ ኃጢአት ስለማይስማማው ፤ የሰዎችን ሁሉ በደል ለመቀበልም ንፁህ መሆን ስላለበት ፤ ይህንም ከአምላክ በቀር የሚያሟላ ባለመኖሩ ፤ ከእሷ ሊወለድ ከመርገም ንፁህ እንድትሆን አደረገ ።
እመቤታችን ነሐሴ 7 ተፀንሳ ግንቦት 1 ሊባኖስ በሚባል ቦታ ተወለደች ። ኢያቄምና ሐና የወለዷት በስለት ስለነበረ በተወለደች ከሶስት ዓመቷ ጀምሮ ለ12 ዓመታት ያህል በቤተ መቅደስ አደገች ። 15 ዓመት ሲሆናት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ መጥቶ አምላክን ትውልጃለሽ ብሎ ባበሰራት ጊዜ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ ብላ ስትቀበል ቃሏን ምክንያት አድርጎ አምላክ ከሥጋዋና ከነፍሷ ከፍሎ ከመለኮቱ ጋር በማዋሃድ መጋቢት 29 ተፀንሶ ታህሳስ 29 ተወለደ ። በዚህም ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ሆነ የሃይማኖታችን ስያሜም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶመባሉ በዚህ ምክንያት ነው ።
የት ተወለደ?
በሚክያስ 5 ፥ 2 ። እንደተነገረው ጌታችን የተወለደው በቤተ ልሔም ከተማ በከብቶች በረት ውስጥ ነው ። ህዝቡ ሁሉ እን ዲጻፍ(እንዲቆጠር) ትእዛዝ ተላልፎ ስለነበረ ዮሴፍ እመቤታችንን ይዞ ሊመዘገብ ከናዝሬት ወደ ቤተ ልሔም በሄደበት ወቅት ከህዝቡ ብዛት የተነሳ ቤት አጥተው በከብቶች በረት ተጠግተው አደሩ በዚያም እያሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰና የዓለም መድኃኒት የሆነ ክርስቶስን በድንግልና ወለደች ። ማቴ 1 ፥ 18 ። ሉቃ 2 ፥ 1 ። በተወለደ ጊዜ አስቀድሞ ትንቢት ተነግሮላቸው የነበሩ ሰብአ ሰገል ፤ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ኮከብ እየመራቸው መጥተው ወድቀው ሰገዱለት ፤ ዕጅ መንሻውንም (ወርቅ ዕጣን ከርቤ) ሰጡት ። ማቴ 2 ፥ 11 ።
በአካባቢው የነበሩ እረኞችም በዙሪያው የሚያበራውን ብርሃን አይተው መልአኩ እየመራቸው ጌታ ከተወለደበት ዋሻ ደር ሰው የጌታን መወለድ አይተዋል ። ከመላእክት ጋር ሆነው ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር፤ በሰማያት ምስጋና ተደረገ በምድርም ሰላም ሆነ ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ በማለት ዘምረዋል ። ሉቃ 2 ፥ 14 ።