ስለፀበል እና እምነት
መፅሀፍ ቅዱሳዊ ትምህርት
ጠበል ማለት በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ህሙማን የሚፈወሱበት ተአምራት የሚደረጉበት ቅዱስ ውሃ
ነው::
ንዕማን ለምጻም እንደነበር እና
በጠበል ሐይል እንደዳነ መጽሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል
“ንዕማንም በፈረሱና በሰረገላው መጣ፥ በኤልሳዕም ቤት
ደጃፍ ውጭ ቆመ። ኤልሳዕም ሂድ፥ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ
ታጠብ፤ ሥጋህም ይፈወሳል፥ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ…… ወረደም፥ የእግዚአብሔርም ሰው
እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ
ብቅ ጥልቅ አለ፤ ሥጋውም እንደ ገና
እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ
ሆኖ ተመለሰ፥ ንጹሕም ሆነ።”2ነገሥት 5፡1-19
እንዲሁም ክርስቶስ በ ዮሐንስ 9:1-8
እንዲሁም ክርስቶስ በ ዮሐንስ 9:1-8
“ኢየሱስ ይህን ብሎ
ወደ መሬት እንትፍ አለ
በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና። ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው… ስለዚህ ሄዶ
ታጠበ እያየም መጣ። “ከመሬት ጭቃ መቀባቱ እምነት መፅሀፍ ቅዱሳዊ እንደሆነ
ይነግረናል
ክርስቶስ በቃሉ ብቻ
አይንህ ይብራልህ ብሎ
ማዳን ይችላል ግን
በብሉይ ኪዳን ህመምተኞች ይፈወሱበት ፣ተአምራት ይደረግበት የነበረው ጠበል በሐዲስ ኪዳንም የተባረከና ፈቅዶ የሰጠን ጸጋ
መሆኑን ለማስረዳት “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ” አለው፡፡
ታዲያ ጠበሎች ሁሉ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም
መጠራት ሲኖርባቸው ለምን የማርያም ጠበል፤የሚካኤል ጠበል ፤የጊዮርጊስ ጠበል ይባላል?
መልሱ አጭር ነው
ይኸውም በጠበሉ ቅዱሳን እንዲታሰቡበት ነው
“እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ
የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል
ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና። በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም
እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም
እሰጣቸዋለሁ።”(ኢሳይያስ 56:4-5 )
እንዲሁም “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” (ምሳሌ 10:7) በሚለው መጽሀፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሰረት በጸበሉ ቅዱሳኑ መጠራታቸው መታሰቢያቸው እንዲሆን ነው፡፡ጠበሉን የፈጠረው መድሐኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እና በጠበሉም አድሮ ህሙማንን የሚፈውሰው እና ተአምራትን የሚያደርገው የእግዚአብሔር ሐይል መሆኑን በደንብ እናውቃለን፡፡
እንዲሁም “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” (ምሳሌ 10:7) በሚለው መጽሀፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሰረት በጸበሉ ቅዱሳኑ መጠራታቸው መታሰቢያቸው እንዲሆን ነው፡፡ጠበሉን የፈጠረው መድሐኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እና በጠበሉም አድሮ ህሙማንን የሚፈውሰው እና ተአምራትን የሚያደርገው የእግዚአብሔር ሐይል መሆኑን በደንብ እናውቃለን፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ