ሰኞ 8 ጁን 2015


‹‹ልጁ እራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል››  1ኛ ቆሮ 15፡22 ምን ማለት ነው

   በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  ውድ እህትና ወንድሞቼ እንደምን አላቹልኝ እንደእግዚአብሔር ፈቃድ ዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እውነተኛ ትርጉም እናያለን ብዙ ጊዜ እስላሞች  ራሳቸውን የይሖዋ ምስሮች በማለት የሚጠሩ አርዮሳውያን እና መናፍቃን ፕሮቴስታንቶች እና ያናገርኳቸው አንዳንድ ተሀድሶዎች ይህንን ጥቅስ በመያዝ ወልድ ሁሉን እንዲገዛ ስልጣንን የሰጠው አብ ነው ነገር ግን ወልድ ሁሉን ላስገዛለት ለአብ ይገዛል ስለዚህ ወልድ ከአብ ያነሰ ስልጣን ነው ያለው ይላሉ፡፡አህዛብ እና አርዮሳውያን ይህንን ቢሉም አይደንቀኝም ነገር ግን የኢየሱስን አምላክነት እናምናለን ሥላሴም እንታመናለን ብለው የሚናገሩ ፕሮቴስታንቶች ይህንን ማለታቸው በጣም የሚያሳዝን እና በአንደበት አምላክነቱን እናምናለን ቢሉም በተግባር እንደካዱት የሚያሳይ ነው፡፡

  ገፀ ንባቡን በማስተዋል ካነበብነው ቅዱስ ጳውሎስ እየተናገረ የመጣው ስለትንሳኤ ሙታን እና ክርስቶስ ሞትን ድል ስለማድረጉ ብሎም ሞት በሁሉም ላይ ስላለመሰልጠኑ ኃይሉንም ስለመሻሩ ነው እስኪ ከቁጥር 20 ጀምረን እንመልከተው ‹‹አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል ሞት በሰው በኩል ስለመታ ትንሳዔ ሙታን በሰው በኩል ሆኗል ሁሉም በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁም በክርስቶስ ህያዋን ይሆናሉና ነገር ግንእያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል ክርስቶስ እንደበኩራት ነው በኋላም በመምጣቱ ለክረስቶስ የሆኑት ናቸው በኋላም መንግስቱን ለአባቱ ለእግዚአብሔር አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ስልጣንንም በሻረ ጊዜ ፍፃሜ ይሆናል ››አለቅነትንም ስልጣንንም በሻረ ጊዜ ፍፃሜ ይሆናል የሚለው የአለም ፍፃሜ የሚሆነው የዚህ አለም ገዢዎች እና አለቆች ስልጣናትን ኃይላትን ስልጣናቸው ተሽሮ መሆኑን ለማስረዳት ነው ምክንያቱም በሌላም ቦታ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሏል ‹‹መጋደላችን ከስጋና ከደም ጋር አይደለምና ከአለቆችና ከስልጣናት ከዚህም ከጨለማ አለም ገዥዎች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ባሉ ከክፋት መንፈሳዊ ሰራዊት ጋር ነው እንጂ››ኤፌ 6፡12 ቀጥሎ ደግሞ ከቁጥር 25-27እንዲህ ይላል ‹‹ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግስ ይገባዋልና የኃለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቷልና ነገር ግን ሁሉ ተገዝቷል ሲባል ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው ››

‹‹ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግስ ይገባዋልና ››የተባለው ለወልድ ነው ጠላቶች የተባሉትም ሞትና ዲያብሎስ ናቸው፡፡ዘፍ 3፡15 እንዲ ተብሏል ‹‹በአንተ እና በሴቲቱ በዘርና በዘርዋ መካከል ጠላትነትን አደርጋለው ››በምፅአት ቀን የሞትና የዲያብሎስ ስልጣን ያከትማል ‹‹ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግስ ይገባዋል ››ሲል ከገዛ በኋላ እንደምድራዊ ሹም ሥልጣኑን አስረክቦ ይወርዳል ለማለት ሳይሆን ለዘለአለም ንጉስ ሆኖ ይኖራል ማለት ነው እዚህ ላይ የገባችው ‹‹እስከ›› ፍፃሜ የለሽ ወይም ዘላለማዊ‹‹እስከ›› ነች ለምሳሌ ‹‹የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አላወለደችም ››2ሳሙ6፡23ይህ ማለት ሜልኮል ከሞተች በኋላ ወልዳለች ለማለት ሳይሆን ለዘለአለም ሳትወልድ ቀረች ማለት ነው ዘፍ 8፡6‹‹ቁራውም ውሀው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይል ነበር ››ይላል እዚህ ላይም ቁራው ውሀው ከጎደለ በኋላ ተመለሰ ለማለት ሳይሆን እስከመጨረሻው ሳይመለስ ቀረ ለማለት ነው ኖህ ቁራው ሳይመለስ ስለቀረ ነው እርግብን የላካት፡፡ አንድም ስልጣኑን ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ የተባለው ጌታ በወንጌሉ ‹‹እረኛው አንድ መንጋውም አንድ››ዮሐ 10፡16 እንዳለ በመጨረሻው ዘመን የክርስቶስ መንግስት በስላሴ መንግስት ይጠቃለላል ማለትም ክርስቶስ ብቻ ይገዛ የነበረው የምድራዊ መንግስት/ሞቶ ስላዳነ ያዳናቸውን ሰዎች እየገዛ ያለው ክርስቶስ ስለሆነ/ያ የብቻው መንግስት በክርስቶስ ተጠቅልሎ የስላሴ መንግስት ይሆናል ማለቱ ነው ፡፡ክርስቶስ መንግስቱን ይተዋል ማለት ግን አላዋቂነት ነው ምክንያቱም በተለያየ ቦታ ለዘለአለም እንደሚገዛ ነው የተፃፈው ሉቃ 1፡33፤ዕብ1፡8

 ቀጥሎ ደግሞ ‹‹ሁሉ ተገዝቷል ሲል ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው ›› ሁሉ የተባለው ከአዳም ጀምሮ ያለው የሰው ዘር ነው ሞት የሰው ዘርን በሙሉ ከትንሽ እስከትልቅ ፃድቃን እና ሀጥእ ሳይል ሁሉን ገዝቶ በሁሉም ላይ ሰልጥኖ ይኖር ነበር ነገር ግን ሞት ሁሉን ገዛ ቢባልም‹‹ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው››ሁሉን ያስገዛለት የተባለው እግዚአብሔር ነው፡፡ሐዋርያው ይቀጥልና ቁጥር 28 ላይ ‹‹ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል››ይህም ማለት የእግዚአብሔር አብ አንድያ ልጁ ወልድ ሁሉን ላስገዛለት ለሞት እሱ ራሱ በስጋው ይገዛለታል ማለት ነው፡፡ሞት ወልድን ሳይቀር በስጋው ይገዛዋል ነው ምክንያቱም እንዲህ ተብሏል ‹‹የባርያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሁኖ ራሱን ባዶ አደረገ……ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳን የታዘዘ ሆነ››ፌል2፡7-8ወልድ ‹‹ለሞት ተገዛ ››ስንል በፈቃዱ ነው በእለተ አርብ በቀራንዮ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው በገዛ ስልጣኑ መለየቱን ለማስረዳት ነው፡፡አስቀድሞ ጌታ እንዲህ ብሏል ‹፣ነፍሴን ደግሞ አነሳት ዘንድ አኖራታለውና›› ……እኔ በፍቃዴ አኖራታለው እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም ላኖራት ስልጣን አለኝ ላነሳት ስልጣን አለኝ፡፡ዮሐ10፡17-18 ስንጠቀልለው ልጁ ራሱ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል ማለት ለአብ ይገዛል ማለት ሳይሆን ከላይ እንዳየነው ሁሉን ላስገዛለት ሞት በፈቃዱ ይገዛል ይህም ተፈፅሟል የመፅሐፍ ልማድ የተደረገውን ገና እንደሚደረግ ያልተደረገውን እንደተደረገ አድርጎ ማውራት ልማድ ነው፡፡

ይቆየን

ወንድማቹ ሸዋፈራው አለነ

ወስብሀት ለእግዚአብሔር

 

 

‹‹ሾልከው በስውር ስለ ገቡ ስለ ሐሰተኞች ወንድሞች››ገላትያ 24/ክፍል አንድ /

" ማደርያውንም በሰማይ የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ" ራእ 136

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ ደም በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ ከውጭም ከውስጥም ፈተና እንደደረሰባት ማንም የሚያውቀው እውነት ነው ለአብነት ያህል ከውስጥ እነ አርዮስ መቅዶንዮስ ንስጥሮስ አውጣኪ …………………………ሌሎችም በመምህርነት ብሎም በጳጳስነት ማእረግ የነበሩ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ኑፋቄን ወደቤተክስስቲያኒቱ አሹልከው በማግባት ምእመኑን ከቤተክርስቲያን እያስኮበለሉ ለዲያብሎስ ሙሽርነት ሲያጯቸው ቤተክርስቲያኒቱንም ለማፍረስ ተፍ ተፍ ሲሉ እንደነበር የሚታወስ ነው እንዲሁም ከውጭ በአላውን ነገስታት በጣዎት አምላኪዎች እና በአህዛብ ባገራችንም በዮዲት ጉዲት እና በአህመድ ግራኝ የደረሰባት ፈተና እና ስደት አሰቃቂ እንደነበር እናስታውሳለን እነዚህ ሰዎች ስማቸውን በመጥፎ ታሪክ መዝግበው አልፈዋል ቤተክርስቲያን ግን እስካሁን አለች ወደፊትም ትኖራለች በክርስቶስ ኢየሱስ አለትነት ላይ ተመስርታለች እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ የገሀነብ ደጆች አይችሏትም እንዳለ ዲያብሎስ ዝናሩን እስከሚጨርስ እንኳን ቢዋጋት ሊያሸንፈት የሚችል አንዳች ሀይል የለም ሰዎች የዲያብሎስን ሽንገላ ተመልክተው ሀይማኖታቸውን ቢክዱ የአጋንንትን ዘመን አመጣሽ ትምህርት እያደመጡ ቤተክርስቲያናቸው ላይ ጦር ቢመዙም ቤተክርስቲያን ዛሬም አለች ወደፊትም ትኖራለች ህያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው ሊያፈርሳት የሚችል አንዳች እደግመዋለው አንዳች ሀይል የለም አራት ነጥብ፡፡ይህንን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ በዚህ በፌስ ቡክ ዳንኤል ዮናስ የተባለ ግለሰብ እና አማሳኝ ተሀድሶአውያን ራሳቸውን ኦርቶዶክስ አድርገው በበግ ተመስለው በተኩላ ባህሪያቸው ቤተክርስቲያኒቱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሔዱባት ይገኛሉ እኔም እንደቤተክርስቲያን ልጅነቴ ቤተክርስቲያኔን እግዚአብሔር በሰጠኝ ፀጋ እና አቅም እንደነ ቅዱስ አትናቴዎስ እንደሌሎችም የቤተክርስቲያን አቃቤ እምነት አባቶች ቤተክርስቲያኔን ከኑፋቄ የመጠበቅ ሀላፊነት ስላለብኝ ብእሬን አንስቼ ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስ ለመስጠት አንድ ብያለው፡፡

ከላይ ስሙን ለመጥቀስ የሞከርኩት ዳንኤል ዮናስ እና ተሀድሶአውኑ የአነ ተክለ ሀይማኖት ገድል እና የተለያዩ ቅዱሳን አባቶች እና እናቶች ገድል እያነሱ ሲሳለቁ ብሎም ሚስጥሩን እና ለምን እንደተባለ ሳይረዱ ገድሉን እያጣመሙ የተባለበትን ሀሳብ ሳይረዱ ወይም ሆን ብለው ለማወቅ ባለመፈለግ ከወንጌል ጋር እያጋጩ ምእመኑንም ግራ እያጋቡ ይገኛሉ መልስ ስጡን ይህ ለምን እንዲህ ተብሎ ተፃፈ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ እየተመለከትን ነው ለዛሬ እንደእግዚአብሔር ፈቃድ በአቡነ ተክለሀይማኖት ገድል ላይ ላነሱት ጥያቄ የመጀመሪያ መልስ በመስጠት ፅሁፌን እጀምራለው ፡፡

ጥያቄ -“ፍሥሐ ለክሙ ወረብሐ ለነፍስክሙ ወመድኃኒተ ለሥጋክሙ ወመንጽሔ ለርስሐትክሙ…. ወሥረይ ለቁሰለ ነፍስክሙ

ትርጉም፦ለእናንተ ተድላ ደስታችሁ ነውና ለሥጋችሁ መጠበቂያ ለነፍሳችሁ መዳኛ ኃጢአታችሁን የሚያነፃ…. ለነፍሳችሁ መድኃኒትነው ብለውታል። (ገድ ተክ ምዕ 214-15)

ይህንን አባታችን የአቡነ ተክለ ሀይማኖት ገድል በመጥቀስ የመልእክቱን ሀሳብ በማጣመም ቤተክርስቲያናችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቤዛነት እና በደሙ የተደረገልንን የሀጢያት ስርየት ዘንግታ አቡነ ተክለሀይማኖት የነፍሳችን መዳኛ እና ቤዛ እንደሆኑ የምታምን አስመስለው ለማቅረብ ሞክረዋል ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እንድታውቁ የምፈልገው ነገር ቢኖር ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን የራሷ የሆነ መፅሐፍ ቅዱሳዊ የድኅነት አስተምህሮ እንዳላት አንድ ሰው የሚድነው በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ በማመን እና የሀጢያት መደምሰሻ በሆነው በደሙ ማስተስረያነት ሀጢያት ስርየት እንደሚገኝ እና በሚስጥራቱ አማካኝነት በሚሰጥ ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ማለትም በቅዱስ ሜሮን እና በቅዱስ ጥምቀት ከክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ ጋር አንድ የምንሆንበት የእግዚአብሔር ልጅነትን ክርስቶስን በማመን ጨምሮ የምናገኝበት በመንፈስ ቅዱስ የምንሞላበት እና የምንነፃበት እንዲሁም በቅዱስ ቁርባን ህይወትን የምናገኝበት እና ከክርስቶስ ጋር የምንዋሀድበት አንድ ሆነን የክርስቶስ አካል ሆነን የምንስራበት ሲሆን ሚስጥረ ሥላሴን አንድነት እና ሶስትነት አምነን የምንኖርበት እንደስራችን እንደሚከፍለን አምነን መልካም ስራ ኖሮን የምንኖርበት እግዚአብሔርን መስለን የምንኖርበት ህይወት እንደሆነ ትእዛዛቱንም ማክበር እንዳለብን ታስተምረናለች ይህም መጽሀፍ ቅዱሳዊ ትምህርት እንደሆነ እነዚህን ጥቅሶች መመልከት ይቻላል /1 ጢሞ 216-261 ጢሞ 411ጢሞ 41፤ዮሐ 35፤ቲቶ 35 ፤ማር 16161 ዮሐ 220 1 227፤ዘጸ 3022-25፤ዮሐ 65፤ዮሐ 654፤ያዕ 214፤ሮሜ 132፤ሮሜ 6 23፤ሮሜ 8 61ዮሐ 3 5፤ማቴ 7 21-23፤ማቴ 25 32-42/ወደፊት እግዚአብሔር ቢፈቅድ ስለመዳን ትምህርት እንማራለን/

ከላይ በአጭሩ እንዳየነው እንደመፅሐፍ ቅዱስ እና እንደ ቤተክርስቲያናችን ትምህርት ሰው የሚድነው ስርየትንም የሚያገኘው በአቡነ ተክለሀይማኖት ነው የሚል ትምህርት የላትም እንዲህ የሚል ትምህርት እንዳላት አድርጎ ማስተማር ሀሰተኝነታችሁን የሚገልጥ ነው ፡፡ታድያ በገድሉ ለምን ለስጋቹ ለነፍሳቹ መዳኛ ሀጢያታችሁን የሚያነጻ ነው ተባለ የሚል ጥያቄ ከተነሳ ለነፍሳችሁ መዳኛ፤ ኃጢዓታችሁን የሚያነፃ ተከለሃይማኖት ነው ሲባል ተክለ ሃይማኖት በጸሎታቸው፤ በትምህርታቸው ወደ መድኃኒቱ፤ ኃጢዓትን ወደሚያነጻው ወደ ክርስቶስ እንድንቀርብ ይረዱናል ማለት ነው።ማለትም አገራችን ኢትዮጵያ በዘመኑ ጣኦትን እና ዳጎንን አምላኪዎች ጠንቋዮች የሞሉበት ጊዜ ነበር በዚህ ጊዜ የተነሱት ፃድቅ አባት ለህዝቡ የወንጌልን ቃል በማስተማር ህዝቡን ከጨለማ ወደብርሀን በመመለስ ለኢትዮጵያ ብርሀን በመሆን የሀጢያት ስርየት የሚገኘው በክርስቶስ ደም እንጂ ጣኦትን በማምለክ እንዳልሆነ በማሳሰብ ለሲኦል ተዘጋጀውን ህዝብ በስብከታቸው ወደጌታቸው በማስጠጋታቸው ክርስቶስን ህይወታቸው እንዲያደርጉ በመስበካቸው ከሲኦል ስለታደጓቸው ትምህርታቸውም ፍሬን አፍርቶ ህዝቡን ክርስቲያን ለወንጌል ታዛዥ ስላደረገው እስካሁን ድረስም ላለው ክርስትና የራሳቸውን አሻራ ስላስቀመጡ በወንጌል ብርሀንነት አገራችን ኢትዮጵያን ስላበሩ ገድሉ ይህንን ለማመልከት ለነፍሳቹ መዳኛ ሀጢያታችሁን የሚያነፃ በሚል ጠቅሶት እናገኛለን፡፡

ግልጽ ለማድረግ አንድ በአንድ ጥቅሱን /ገድሉን እንየው/

ለእናንተ ተድላ ደስታቹ ነውና፡-ወንጌል ማለት የምስራች ማለት እንደሆነ ሁሉ ወንጌልን አያውቅ የነበረው ህዝብ ወንጌል ሲሰማ ምስራቹን ሲያደምጥ የሚሰማውን የመንፈስ እና የነፍስ ደስታ ከአባታችን ስብከት እንደሚያገን ልብ ይሏል፡፡

ለስጋቹ መጠበቂያ ለነፍሳቹ መዳኛ ሀጢያታችሁን የሚያነጻ -ስጋችን እና ነፍሳችንን በወንጌል ቃልነት ሞልተውት ክርስቶስን በቃላቸው እና በፀሎታቸው አሳስበውት ስጋችን ከሀጢያት ርኩሰት እንዲነፃ እንዲከለከል ነፍሳችን ክርስቶስን በማወቅ እንድትድን ሀጢያታችንን የሚያነጻ ማለትም ወደክርስቶስ እንድንቀርብ እንደሚያሳስቡ እንዲሁም ሀጢያታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ይቀርላችኋል ያለውን የወንጌል ቃል ልብይሏል ማለትነው ፡፡

ለነፍሳቹ መድሀኒት፡-ክርስቶስን ስላሳወቁ በክርስቶስ የምናገኘውን ድነት ያመላክታል፡፡

ባጠቃላይ ከላይ እንዳልነው ለነፍሳችሁ መዳኛ፤ ኃጢዓታችሁን የሚያነፃ ተከለሃይማኖት ነው ሲባል ተክለ ሃይማኖት በጸሎታቸው፤ በትምህርታቸው ወደ መድኃኒቱ፤ ኃጢዓትን ወደሚያነጻው ወደ ክርስቶስ እንድንቀርብ ይረዱናል ማለት ነው። ከዚህ ውጪ አንረዳውም ፡፡

ማጠቃለያ፤-

ልብ የሚባልበት ጥቅስ፡-

-የዮሐንስ ወንጌል
2023
ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል አላቸው።
 

ሀጢያት ይቅር የሚል ከርስቶስ እንደሆነ እሙን ቢሆንም ቅዱሳኑም ሀጢያትን ይቅር የማለት ስልጣን እንዳላቸው ልንገነዘብ ያስፈልጋል

-የማቴዎስ ወንጌል

514
እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።

ኢየሱስ የአለም ርሀን እንደሆነ ቅዱሳኑም የአለም ብርሀን ብሎ ጠርቶአቸዋል

ቅዱሳኑን የምናስባቸው፡-

1.በረከት እናገኛለን "የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ107

2.በቃል ኪዳናቸው እንጠቀማለን "ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርግሁ" መዝ 883

3.ከሕይወታቸው እንማራለን "የኑሮአችውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው" ዕብ 137

4.የእግዚአብሄርን ጸጋ እናደንቃለን "እግዚአብሄር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው" መዝ 6735

ጥቂቶቹ ናቸው ታድያ ቅዱሳኑን ማሰብ በአላቸውን ማክበር ይሄን ያህል በረከት ካለው ሃዋርያው እንዳለው ጊዜ አይበቃንም እንጂ ቢቻለን አረፍተ ዘመን እስኪገታን ለትውልዱ ስለቅዱሳኑ ብናወራ ምንኛ መልካም በሆነልን
".........
ስለዳዊት ስለሳሙኤልም ስለነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና" ዕብ1132

ይቀጥላል

ወንድማቹ ሸዋፈራው አለነ

"መልካሙን የምስራች የሚያውሩ እግሮቻቸው እን ዴት ያማሩ ናቸው" ኢሳ527

ወስብሀት ለእግዚአብሔር

ሊያስቆመን የሚችል አንዳች ሀይል የለም ቁርጠኛ የተዋህዶ ልጆች ነን